Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሳሰላስለው

Saselaselew

ትራክ 1 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ምን ልበል ምን ልናገር ቃላትም አጠረኝ

የሞትን አዋጅ ሽሮ በሕይወት ኑር ሲለኝ

ምህረቱ እንደፀና የሚያውቀኝ ያውቀው የለ

ያ ክፉ እንዳይጎዳኝ ቁጣውን ከለከለ

እኔማ ሳሰላስለው እኔማ የትናንቱን (፪x)

እኔማ ምክንያት ሆነኝ እኔማ ለማመስገን (፪x)

እኔማ እንደሌላ ሰው እኔማ ዝም አያሰኘኝ (፪x)

እኔማ ሀገር ያውቅ አይደል እኔማ እንደረዳኸኝ (፪x)

የተጠበቁ ጉድጓዶች ምንጫቸው ነጠፈ (፬x)

ያም ሄደ እያለፈ ይሄም ሄደ እያለፈ (፬x)

ብቻውን ህዝቡን የመራ በደረቁ ምድር (፬x)

ምንኛ ታማኝ ነው ታማኙ እግዚአብሔር (፬x)

አለኝታዬ (፬x) መከታዬ (፬x)

ቁምነገር ተገኘበት አይጠቅምም የተባለው

የሰማይ የምድር ጌታ ከሱ ጋር አብሮ ዋለ

በንጉስ ገበታ ላይ ተገኘ በክብር

ምስኪኑን የሚያነሳ ማነው እንደ እግዚአብሔር

እኔማ ሳሰላስለው እኔማ የትናንቱን (፪x) ያለፍኩትን (፪x)

እኔማ ምክንያት ሆነኝ እኔማ ለማመስገን (፪x)

እኔማ እንደሌላ ሰው እኔማ ዝም አያሰኘኝ (፪x)

እኔማ ሀገር ያውቅ የለ/እኔማ እንደረዳኸኝ (፪x)

ሁሉም ያውቅ የለ (፪x)

ያሰብኩት እንዳይሞላ እንቅፋት ሲገጥመኝ

ከፊቴ እየቀደመ ገለል አረገልኝ

ማዕበሉ እንዳያሰጥመኝ ንፋሱን ሲገስፀው

አይኔ አይቷል በዘመኔ ፍጥረታት ሲታዘዘው

እኔማ ሳሰላስለው እኔማ የትናንቱን (፬x) ያለፍኩትን (፪x)

እኔማ ምክንያት ሆነኝ እኔማ ለማመስገን (፬x)

እኔማ እንደሌላ ሰው እኔማ ዝም አያሰኘኝ (፬x)

እኔማ ሀገር ያውቅ የለ እኔማ እንደረዳኸኝ (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ