Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ከሥም ሁሉ በላይ

Kesem Hulu Belay

ትራክ 10 · 5:24 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

(ማን ልበለው ጌታን

ማን ልበለው ኢየሱሴን) X፪

(ከስም ሁሉ በላይ ስም አለው

ለእርሱ ማይገዛ እስኪ ማነው

ሁሉን በፈቃዱ የሚያደርገው

አምላኬ የጌቶች ጌታ ነው) X2

(ኧረ ስንቱን ስንቱን አለፍኩኝ

በምህረቱ ብዛት ደግፎኝ

ቢነሳ ቢነገር ውለታው

አያልቅም ካይምሮ በላይ ነው) X2

እንካ ተንሰራፋ በልቤ ዙፋን ላይ

ምን እኔነት አለኝ ሁሉ ያንተ አይደል ወይ

በተቀደሰው ተራራዬ ላይ

አንተው ድመቅበት ሳይኖርህ ከልካይ

በሁሉ ላይ ሾምኩህ በሁሉ ነገር ላይ

ሁሉም ይወቅልኝ (መሆንክን የበላይ) X2

አንደበቱን ከፍቶ ፍጥረት ያመስግንህ

በሰማይ በምድር (አቻ አልተገኘልህ) X2

(ያፍህ ቃል ውድዬ ጣፋጭ ነው

ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው

ሳላነሳህ ውዬ አላድርም

ከአንተ ውጪ እርካታ የለኝም) X2

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ