በልጅነት
Belejenet
ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔም እንዲህ እንዲህ ወግ ደረሰኝ
ከመቅበዝበዝ እሱ በቃ ሲለኝ
ያ መራራ ሕይወቴ ጣፈጠ
በኢየሱሴ ታሪክ ተለወጠ
አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ
አይቼዋለሁ ኢየሱሴን ለኔስ ልዩ ነው
እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ
እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን እኔ አውቀዋለሁ
አይዞህ ባየለኝ ጌታ እርሱ ባይረዳኝ
ማንስ ሊጎበኘኝ ማንስ ሊቀርበኝ
በቃ ሲል አበቃ ያ ዘመን አለፈ
ጭጋጉ ከፊቴ ይኸው ተገፈፈ
ለእኔስ ብዙ ብዙ ብዙ አድርጎልኛል
ያደላል ብላችሁ ማን ይቀየመኛል
ከናት ካባት በላይ ስለተመቸኝ
እንደሱ ያለ የለም ሁሌ እላላሁኝ
አዝማች · Chorus
ያ መራራ ቀን ያለፈው በእርሱ ነው (፪x)
ጭጋጉ የተገፈፈው በሱ ነው (፪x)
ማን ልበለው ምን ልበለው (፪x)
በምን ቋንቋ በምን አንደበት
ይነገራል የእርሱ ደግነት
ቁጥር 2 · Verse 2
እኔስ ገና ገና በልጅነት
አይቻለሁ የጌታዬን ምህረት
ሲርበኝም ከእጁ በልቻለሁ
ያንን ሁሉ መች እዘነጋለሁ
አይቼዋለሁ ጌታን አይቼዋለሁ (፪x)
አይቼዋለሁ የሱሴን ለኔስ ልዩ ነው (፪x)
እኔ አውቀዋለሁ ጌታን እኔ አውቀዋለሁ (፪x)
እኔ አውቀዋለሁ ኢየሱሴን እኔ አውቀዋለሁ (፪x)
አዝማች · Chorus
ያ መራራ ቀን ያለፈው በእርሱ ነው (፪x)
ጭጋጉ የተገፈፈው በሱ ነው (፪x)
ማን ልበለው ምን ልበለው (፪x)
በምን ቋንቋ በምን አንደበት
ይነገራል የእርሱ ደግነት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ