ንገስልኝ
Negeselegn
ትራክ 9 · 5:37 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔርን በመተማመን ተግተው የሚጠባባቁ (፪x)
ከመልካም ነገር አይጎድሉም በመከራ ቀን አይወድቁ (፪x)
ለደካሞችም ኃይላቸው ነውና እንደሚለው ቃሉ (፪x)
የረዳችሁ ያገዛችሁ ከእኔ ጋር ክበር በሉ (፪x)
አዝማች · Chorus
ክበርልኝ (፪x)
በአንተ ነውና ያማረብኝ
ንገስልኝ (፪x)
በአንተ ነውና ሰው የሆንኩኝ
ክበር ክበርልኝ (፪x)
ንገስ ንገስልኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቆይቼ ደጅ ጠናሁት እሱም ዘንበል አለልኛ (፪x)
ታምኜው አላሳፈረኝ ጌታ እውነተኛ ዳኛ (፪x)
ጠብቆ ያልከሰረ የወጣ ከጭንቅ ከማጡ (፪x)
ያክብረው በዝማሬ ከእኔ ጋር ክብርን ያምጡ (፪x)
አዝማች · Chorus
ክበርልኝ (፪x)
በአንተ ነውና ያማረብኝ
ንገስልኝ (፪x)
በአንተ ነውና ሰው የሆንኩኝ
ክበር ክበርልኝ (፪x)
ንገስ ንገስልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
ንገስ ንገስልኝ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ