ነገሥታት ቢቀየሩ
Negestat Biqeyeru
ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ሕዝብም ሁሉ ይሄዳል በያምላኩ (፪x)
አልተለቁም በሚያልፈው የተመኩ (፪x)
እኛም ደግሞ ዘላላም እንሄዳለን
አናፍርም አንከሰርም ጌታን ታምነን
አምላካችን መጠጊያችን (፪x)
በመከራ ረዳታችን (፪x)
ቢነዋወጥ ምድር በሞላ (፪x)
ያድነናል የእኛስ ከለላ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ነገሥታት ቢቀየሩ አንዱ ባንዱ ቢተካ
እፎይ ብሎ ላያድር ውጥረቱ ላያበቃ
ዘመን ያመጣው ችግር ትውልድን ሲያሸብረው
ለፍጥረት መታመኛ ጌታ አለ ለታመነው
አዝማች · Chorus
ሕዝብም ሁሉ ይሄዳል በያምላኩ (፪x)
አልተለቁም በሚያልፈው የተመኩ (፪x)
እኛም ደግሞ ዘላላም እንሄዳለን
አናፍርም አንከሰርም ጌታን ታምነን
አምላካችን መጠጊያችን (፪x)
በመከራ ረዳታችን (፪x)
ቢነዋወጥ ምድር በሞላ (፪x)
ያድነናል የእኛስ ከለላ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰው ባለው ምን ቢኮራ ዓይኑን ካምላኩ አንስቶ (፪x)
ቢደገፍ በሚጠፋው መገኛውን ዘንግቶ (፪x)
የቆመ የመሰለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ (፪x)
ቢናወጥ ምድር ሰማይ ጌታ ነው የሚያዘልቅ (፪x)
ሃሌሉያ ኦ ሃሌሉያ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ