ማዕረጉ
Maeregu
ትራክ 12 · 5:38 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዝም ቢል አንደበት እጆችም ባይዘረጉ
አይቀንስ ችሎታው አይቀንስ ማዕረጉ
የሰማይ ቅዱሳን ደግሞም መላዕክቱ
ሁሌ ይቀኙለታል ላፍታም ሳይታክቱ
ካፅናፍ እስካፅናፍ ተርፏል የሚያመልከው
የፍቅሬን ነው እንጂ እርሱ ምን ሊጎድለው
የዳንኩ እኔ ያመለጥኩ እኔ
ተፈወስኩ እኔ የሞተው ለእኔ
አዝማች · Chorus
እቀኛለሁኝ ለመድህኔ (፪x)
እዘምራለሁ ለመድህኔ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ቢወደድ አይበዛ
ቢፈቀር አይበዛ
ክበር ቢባል አይበዛ
ቢመሰገን አይበዛ
ነፍሴን ከሞት ስለገዛ
ክበር ቢባል ከቶ አይበዛ
ነፍሴን ከሞት ስለገዛ
ክበር ቢባል ከቶ አይበዛ
አከብርሀለሁ (፬x)
እወድሀለሁ (፬x)
እንካ ተቀበለው አምልኮዬ ይኸው
እንካ ተቀበለው ዝማሬየም ይኸው
እንካ ተቀበለው ምስጋናዬ ይኸው
እንካ ተቀበለው መጓደዴም ይኸው
ቁጥር 3 · Verse 3
ዝም ቢል አንደበት እጆችም ባይዘረጉ
አይቀንስ ችሎታው አይቀንስ ማዕረጉ
የሰማይ ቅዱሳን ደግሞም መላዕክቱ
ሁሌ ይቀኙለታል ላፍታም ሳይታክቱ
ካፅናፍ እስካፅናፍ ተርፏል የሚያመልከው
የፍቅሬን ነው እንጂ እሱ ምን ሊጎድለው
የዳንኩ እኔ ያመለጥኩ እኔ
ተፈወስኩ እኔ የሞተው ለእኔ
አዝማች · Chorus
እቀኛለሁኝ ለመድህኔ (፪x)
እዘምራለሁ ለመድህኔ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ