ምሥጋናዬ ነህ
Mesganayie Neh
ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ተራራው ከፊቴ እንደሰም ቀለጠ ምሥጋናዬ ነህ
ቃልህም ሲወጣ ጫካው ተገለጠ ምሥጋናዬ ነህ
እግሮቼም ፀኑልኝ እንደዋላ እግር ምሥጋናዬ ነህ
ረዳት ሆነኸኛል አምላኬ ክበር ምሥጋናዬ ነህ
አዝማች · Chorus
ልሰዋ የምሥጋናን መስዕዋት
ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት
ላክብርህ እኔ ደጋግሜ
ቁጥር 2 · Verse 2
ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ 2x
አቤቱ ተደንቄያለሁኝ እና (፪x)
ልሰዋ ምሥጋና (፬x)
ምህረትህ ከሕይወት በርግጥም ይበልጣል ምሥጋናዬ ነህ
ደጅ ጥናት የለም በፍጥነት ያነሳል ምሥጋናዬ ነህ
ድንጋይ ተደርድሮ ሞት ሲጠብቃት ምሥጋናዬ ነህ
ሀፍረቷን ሸፍነህ ሰላም ሂጂ አልካት ምሥጋናዬ ነህ
አዝማች · Chorus
ልሰዋ የምሥጋናን መስዕዋት
ሆነኸኝ አይቻለሁ አባት
ላክብርህ እኔ ደጋግሜ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከፍ በል ላዚም ፊትህ ቆሜ (፪x)
አቤቱ ተደንቄያለሁኝ እና (፪x)
ልሰዋ ምሥጋና (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ