ያድናል
Yadenal
ትራክ 7 · 5:19 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታ ነው ቢጎድልም ቢሞላ
በሕይወቴ የለም ከእርሱ ሌላ
ችግሩ ከቦ ቢያስጨንቀኝ
ከርስቴ ማን ሊነቀንቀኝ
አዝማች · Chorus
እኔ አለሁ (፪x)
አልነሳም ከመሰዊያው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ጌታ ነው ቢጎድልም ቢሞላ
በህይወቴ የለም ከሱ ሌላ
ችግሩ ከቦ ቢያስጨንቀኝ
ከርስቴ ማን ሊነቀንቀኝ
አዝማች · Chorus
እኔ አለሁ (፪x)
አልነሳም ከመሰዊያው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እየተፀለየ እየተዘመረ
ከቀደመው ይልቅ ችግሩ ጨመረ
ሰባት እጥፍ ቢሆን ጨምሮ ጨምሮ
እግዚአብሔር ያድናል ችግርን ሰባባሮ
እየተፀለየ እየተዘመረ
ከቀደመው ይልቅ እሳቱ ጨመረ
ሰባት እጥፍ ቢነድ ጨምሮ ጨምሮ
እግዚአብሔር ያድናል የእሳትን ኃይል ሰብሮ
ቁጥር 4 · Verse 4
ያድናል ዛሬም/እኮ ያድናል
ለጌታ ምን ይሳነዋል
ሕያው ነው አልተለወጠም
ያድናል ለዘላለም (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
የሰጠ እርሱ አይደለም ወይ
ቢነሳ ከልካይስ አለው ወይ
አትበይ እንደሰነፎች
ከሁሉ ጌታ ነው የሚመች
አዝማች · Chorus
እኔ አለሁ (፪x)
አልነሳም ከመሰዊያው (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እንዲህ ነው አይባል የጌታ አሰራሩ (፪x)
ፈፅሞ አይታማም ግሩም ነው በምክሩ (፪x)
ቢዘገይም እንኳን በጊዜው ይደርሳል (፪x)
ካለቀሰ ሁሉ እንባ ይታበሳል (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
ያድናል ዛሬም ያድናል
ለጌታ ምን ይሳነዋል
ሕያው ነው አልተለወጠም
ያድናል ለዘላለም
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ