ድረስለት
Dereselet
ትራክ 6 · 5:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እልፍ ጥያቄ እልፍም ችግር
ታቅፎ የኖረ ሳያንገራግር
ችግሩን ቻል አድርጎ
ጌታ ይበልጣል ብሎ
ሲያመልክ ባደባባይ
ይሰማ በአንተ ዘንድ ይታይ
አዝማች · Chorus
ይረዳል ይበል ተረድቶ
ያግዛል ይበል ታግዞ
ቁጥር 2 · Verse 2
ድረስለት ለእንዲህ ዓይነቱ ሰው (፪x)
ባዶውን እንዲሁ አትመልሰው (፪x)
ሲማፀን በቆመበት ስፍራ (፪x)
አለሁ በለው ስምህን ሲጠራ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይረዳል ይበል ተረድቶ
ያግዛል ይበል ታግዞ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከወገኖቹ ከሀገር እርቆ
በባእድ ምድር ሚኖር ተሳቆ
ያሰበው ባይሞላለት ሲያለቅስ በያለበት
ራራ ስማው አቤቱ
አለሁ በል ለእንዲህ ዓይነቱ
አዝማች · Chorus
ይረዳል ይበል ተረድቶ
ያግዛል ይበል ታግዞ
ቁጥር 4 · Verse 4
ድረስለት ለእንዲህ አይነቱ ሰው (፪x)
ባዶውን እንዲሁ አትመልሰው (፪x)
ሲማፀን በቆመበት ስፍራ (፪x)
አለሁ በለው ስምህን ሲጠራ (፪x)
አዝማች · Chorus
ይረዳል ይበል ተረድቶ
ያግዛል ይበል ታግዞ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ