አንድ ነገር አውቃለሁ
And Neger Awqalehu
ትራክ 5 · 15:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ፀጋህን እንጂ ጽድቄን አልቆጥር
ከሰጠኸኝ በላይ ምንም አልጨምር
የማልጠቅም ባርያ ታሪክ የሌለኝ
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ እንዳዳነኝ
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ይከሰኛል
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማን ይቃወመኛል
ቁጥር 2 · Verse 2
ሞትና እርግማን ተጭኖኝ ነበር
ነፍሴን አጉብጧት የሀጥያት ቀንበር
የዓለም ብርሀን ኢየሱስ ሲመጣ
ጨለማዬ ተወገደ ለእኔም ብርሀን ወጣ
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ይከሰኛል
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማን ይቃወመኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
አድራሻ የለኝ መነሻ ስፍራ
ሥሜ አይታወቅ ዘሬ አይጠራ
እንዳላሰብኩት በውን በህልሜ
ከነአብርሀም ከነዳዊት ተመዝግቧል ሥሜ
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ይከሰኛል
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማን ይቃወመኛል
ቁጥር 4 · Verse 4
ብርሀኔና መድኃኒቴ ነው
ታዲያ እሱን አልፎ ሚነካኝ ማነው
ማንስ ቢመጣ ምን ያደርገኛል
የጸና ግንብ የእሳት አጥር ኢየሱስ ሆኖኛል
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ይከሰኛል
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማን ይቃወመኛል
ቁጥር 5 · Verse 5
ከተደረገው ከሆነው ነገር
ጥቂቱም አይገባኝም ነበር
ሞልቶ እስከሚፈስ አየሁ ምህረቱን
ሁሉ ከእርሱ ሁሉ በእርሱ ለእርሱ ክብር ይሁን
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማንስ ይከሰኛል
አንድ ነገር ግን አውቃለው ኢየሱስ ወዶኛል (፫x)
ማን ይቃወመኛል
ሀሌሉ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን
ቁጥር 6 · Verse 6
ሁሉን የሚገዛ ስራው ታላቅና ድንቅ
ይገባዋል ለዘለዓለም እኛ ልናንስ እርሱ ሊልቅ
በመንገዱ ጻድቅ በፍርዱ እውነተኛ
ለቃሉ ታማኝ ነው ለስሙ ቀናተኛ
አዝማች · Chorus
ሀሌሉ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን
ቁጥር 7 · Verse 7
ከትንሳኤ በኩር ከፍጥረት መጀመሪያ
አልፋና ኦሜጋ መክፈቻና መዝጊያ
የቤተ ክርስቲያን ራስ ያለና የሚመጣ
የጌቶች ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው
አዝማች · Chorus
ሀሌሉ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን
ቁጥር 8 · Verse 8
የርስታችን መያዢያ ለቤዛም ቀን ያተመን
ወደ እውነት የሚመራን በመከራም ሚያቆመን
በሀይሉ የሞላ ስጦታውን ያደለን
ከሰማይ የተላከ መንፈስ ቅድስ አለን
አዝማች · Chorus
ሀሌሉ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን
ቁጥር 9 · Verse 9
እግዚአብሔር አብ ልጁን ሰጠን እግዚአብሄር ወልድ እራሱን ሰጠን
መንፈስ ቅዱስ ቃሉን ሰጠን ቃሉም እኛን ለወጠ
ቸር አምላክ ባለጸጋ ዘወትር እጁን የዘረጋ
አያልቅበት ሁሌ ሙሉ ሀሌ ሀሌሉያ በሉ
አዝማች · Chorus
ሀሌሉ ሀሌሉያ (፬x)
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን
ቁጥር 10 · Verse 10
አንድ ሰው ነካኝ በድንገት አንድ ሰው ነካኝ
ቁጥር 11 · Verse 11
እስራት ነበረኝ ፈታኝ ድካም ነበረኝ አነቃኝ
ጥማት ነበረኝ አረካኝ አንድ ሰው ነካኝ
በርጠሚዎስ እኔነኝ ዘመድ የራቀኝ
እድሜ ልኬን በልመና አለም ያወቀኝ
የመንገድ ጉቶ እንቅፋት ሁሉም ሲሰድበኝ
እኔም ወግ ሊደርሰኝ ሆነ አምላክ ሊያስበኝ
የዳዊት ልጅ ሆይ ና ማረኝ ብዬ ብጣራ
ኢየሱስ መጣ ዳሰሰኝ አይኔን አበራ
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ነካኝ በድንገት ኢየሱስ ነካኝ
እስራት ነበረኝ ፈታኝ ድካም ነበረኝ አነቃኝ
ጥማት ነበረኝ አረካኝ ኢየሱስ ነካኝ
ቁጥር 12 · Verse 12
ሽባ ነበረ ማይሰራ እግሬና እጄ
ሰላሳ ስምንት አመታት ተቆራምጄ
መላክ ሲመጣ ውሀውን ሲያንቀሳቅሰው
ቀድሞ የደረሰ ሲፈታ ሲሄድ ስንት ሰው
በድሌ ሳዝን በሰው ዘንድ እንደተረሳው
ኢየሱስ መጣ አስነሳኝ እኔም ተነሳው
አዝማች · Chorus
ኢየሱስ ነካኝ በድንገት ኢየሱስ ነካኝ
እስራት ነበረኝ ፈታኝ ድካም ነበረኝ አነቃኝ
ጥማት ነበረኝ አረካኝ ኢየሱስ ነካኝ
ቁጥር 13 · Verse 13
ለአስራ ሁለት አመታት እንባ እንደ ጅረት
ባለ መድሃኒት አልቀረኝ ስንት ሀገር ዙረት
ትርምስ አየሁ በድንገት ሳልፍ በመንገዱ
በብዙ ሺዎች መካከል ተከቧል አንዱ
ጌታ መሆኑን አውቄ ልብሱን ብነካ
መከራዬ በድንገት ምንጩ ተዘጋ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ