በአዝመራ ጊዜ መኝታ
Beazmera Gizie Megneta
ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በአዝመራ ጊዜ መኝታ በጽሞና ጊዜ ጫጫታ
የሰልፍ ነው የድል ይህ ሁሉ እልልታ
ጌታ ሆይ ማስተዋልን ስጠን ጊዜ እንዳያመልጠን
ቁጥር 1 · Verse 1
መከራው እግሩን ከማውጣቱ አቆምን መንበርከክ በፊቱ
የጸሎት መሰዊያ አፈረስን መስሎናል ሰማይ የደረስን
የምድረበዳው ትውልድ በውነ በወጉ አያውቅም ጦርነት
መሬትን አልረገጠም በእግሩ አታሎት እሩጫው ግርግሩ
አዝማች · Chorus
በአዝመራ ጊዜ መኝታ በጽሞና ጊዜ ጫጫታ
የሰልፍ ነው የድል ይህ ሁሉ እልልታ
ጌታ ሆይ ማስተዋልን ስጠን ጊዜ እንዳያመልጠን
ቁጥር 2 · Verse 2
እርስ በርስ እየተሟሟቅን ነፍሳትን ተዘርፈን አለቅን
መርከቡ መልህቁን ዘርግቶ ይጣራል ተሳፋሪ ጠፍቶ
ይቺ አለም ካልደረስንላት ጨውና ብርሀን የላት
ህመሟ ሄደ እየቀጠለ መድሀኒት በእጃችን አለ
አዝማች · Chorus
በአዝመራ ጊዜ መኝታ በጽሞና ጊዜ ጫጫታ
የሰልፍ ነው የድል ይህ ሁሉ እልልታ
ጌታ ሆይ ማስተዋልን ስጠን ጊዜ እንዳያመልጠን
ቁጥር 3 · Verse 3
ተባባልን እኔ ካንተ አላንስም ታወቅን ጌታ ባልሰጠን ሥም
ተራራቅን አጥር እያጠበቅን ለፍቅር ክፍያ ጠየቅን
በእልህ ሳይሰፋ ገደሉ ለበደልን ላጎደልነው ሁሉ
ንስሀ እንገባለን ፊትህ ጌታ ሆይ ይምጣልን ምህረትህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ