ዲያቢሎስ ምነው ቸኮለ
Diyabilos Menew Chekole
ትራክ 10 · 4:41 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ዲያቢሎስ ምነው ቸኮለ ሊውጠን እየከጀለ
መሰለኝ ቀኑ ሊደርስ የሰይጣን መንግስት ሊፈርስ
በእርግጥ ቀኑ ደርሶ ነው የሚይዘው ግራ ገብቶት ነው (፫x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የገባው ደረቱን ነፍቶ ነጋሪት ከበሮ መቶ
ሲወጣ በጣር ተይዞ በጌታ ኢየሱስ ስም ታዞ
አይተናል ዛሬም ይሆናል የኢየሱስ ስሙ ያድናል
አዝማች · Chorus
ዲያቢሎስ ምነው ቸኮለ ሊውጠን እየከጀለ
መሰለኝ ቀኑ ሊደርስ የሰይጣን መንግስት ሊፈርስ
በእርግጥ ቀኑ ደርሶ ነው የሚይዘው ግራ ገብቶት ነው (፫x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሌባ ነው ነፍስን ይሰርቃል ከህይወት መንገድ ያርቃል
አይገባም በዋናው በር ይያዛል መስኮት ሲሰብር
ሲሸፍት እንደ ልማዱ ደቆሰው ኢየሱስ በክንዱ
አዝማች · Chorus
ዲያቢሎስ ምነው ቸኮለ ሊውጠን እየከጀለ
መሰለኝ ቀኑ ሊደርስ የሰይጣን መንግስት ሊፈርስ
በእርግጥ ቀኑ ደርሶ ነው የሚይዘው ግራ ገብቶት ነው (፫x)
ቁጥር 3 · Verse 3
አድራሻው አመድ አተላ እንደ ከብት አሳር ሲያበላ
የለውም ክብር ማእረግ አያውቅም ሰው ማሳደግ
ኢየሱስ አዳነን ከእጁ ሆ በሉ ስሙን አውጁ
አዝማች · Chorus
ዲያቢሎስ ምነው ቸኮለ ሊውጠን እየከጀለ
መሰለኝ ቀኑ ሊደርስ የሰይጣን መንግስት ሊፈርስ
በእርግጥ ቀኑ ደርሶ ነው የሚይዘው ግራ ገብቶት ነው (፫x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለመስቀል እንጨት ሲቆርጥ መዶሻ ሚስማር ሲሰጥ
መቃብር ድንጋይ ሲገጥም ዘብ ሲያቆም ማእተም ሲያትም
ፈርቶ ነው ይህ ሁሉ አበሳ አልቀረም ኢየሱስ ተነሳ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ