Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በቀኑ መጨረሻ

Beqenu Mecheresha

ትራክ 3 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ

ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ

አንተን በመፍራት አሳድገኝ

ቅጠሌን አይተው የተመሰጡ

ፍሬን ፍለጋ ቤቴ ስመጡ

በጣፋጭ ዜማ እየጠራሁኣቸው

ያለ ዉሃ እንዳሸኛቸው

ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ

ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ

አንተን በመፍራት አሳድገኝ

ስምህ ተጠርተው ድንቅን ስሰራ

የኔ ገድል እንዳይወራ

መድረኩም እንኳ ብነቃነቅ

አንተን አክብሬ ራሴን ልናቅ

ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ

ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ

አንተን በመፍራት አሳድገኝ

የውርንጫዋ የስራ ድርሻ

ወደ ኢየሩሳሌም መድረሻ

ጨርቅ ብነጠፍ ሆሳዕና ብባል

ክብር ስግደትም ላንተ ይገባል

ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ

ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ

አንተን በመፍራት አሳድገኝ

ባመጽ ተወልደን በኃጢኣት አድጋናል

በጎውን ነገር ማን ያሳየናል

በሚለው ትውልድ መካከል ስገኝ

እውነትን ገላጭ ብርሃን አድርገኝ

ጌታ ሆይ በየቀኑ መጨረሻ

ለትውልድ መፈወሻ አድርገኝ

አንተን በመፍራት አሳድገኝ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ