Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አምንሃለሁ

Amnehalehu

ትራክ 8 · 8:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፀጋህ ለእኔ በዝቶ እዚህ ደርሻለሁ

አንተ ከቆምክልኝ ሌላ ምን እሻለሁ

የገፋኝ ተገፍቶ የወጋኝ ተወጋ

ያልያዝኩትን ልያዝ እጆቼን ልዘርጋ

ባለሁበት አልሂድ ጊዜ አይለፍብኝ

እስቲ ከመንፈስህ እፍ በልብኝ

አምንሀለው ጌታ አምንሀለው

ቃልህን ስታከብር አይቻለው

አምንሀለው ጌታ አምንሀለው

ከግብጽ ወጥቼ ምድረበዳ ዘለኩ

ባህር ተሻግሬ ዮርዳኖስን አለፍኩ

እያሪኮ በራፍ ቆሜ ለምን ላልቅስ

የትላንቱን ጌታ ልታመን ይልቅስ

የግብጽን ሰራዊት ባህር ያሰጠመ

እግዚአብሄር ብርቱ ነው ዛሬም አልደከመም

አምነዋለው ጌታን አምነዋለው

ቃልኪዳኑን ሲያከብር አይቻለው (፪x)

አምነዋለው ጌታን አምነዋለው

የኤናቄል ልጆች ቁመናቸው ሎጋ

ውስጣቸው ባዶ ነው በእምነት ልጠጋ

በእነርሱ አይን ስታይ አንበጣ መስላለው

በውስጤ ያለው ግን ኃያል እግዚአብሔር ነው

እስከመቼ ድረስ ፈርቼ ልኑር

ተሻግሬ ልውረስ የተስፋይቱን ምድር

አምነዋለው ጌታን አምነዋለው

ቃልኪዳኑን ሲያከብር አይቻለው (፪x)

አምነዋለው ጌታን አምነዋለው

እምነት ከመስማት ነው መስማትም በቃሉ

ለሚመረምሩት መልስ አለው ለሁሉ

ቃሉን እያነበብኩ ተስፋውን ባላምን

ጊዜ ማጥፋት እንጂ መመላለስ ለምን

በአባቶቼ ዘመን ድንቅን ያደረገው

የጠራኝ እግዚአብሄር የጌቶች ጌታ ነው

አምነዋለው ጌታን አምነዋለው

ቃልኪዳኑን ሲያከብር አይቻለው (፪x)

አምነዋለው ጌታን አምነዋለው

ከስሞች በላይ ስሙ ሀያል በሰማይ በምድር ሁሉን ያያል

የተዋረደን ከፍ ያደርጋል ታናናሾችን ያሳድጋል

ሁሉ በእጁ ነው በችሎታው ከልካይ የለውም የሚገታው

ምስጋና ክብር ሞገስ ለርሱ ለዘለዓለም ለንጉሱ

መውደቅ ለጠላቴ መዋረድ ለሰይጣን

መድከም ለስጋዬ መሸነፍ ለዓለም

ክብር ግን ለኢየሱስ ይሁን ለዘለዓለም

በሰማይ ይሁን በምድር ላይ አቻ የለውም እሱን መሳይ

እርሱ ብቻውን ጌታ ነው ታናሽም ታላቅ የሌለው

ስጋ በፊቱ ይዋረድ ዲያቢሎስ አይቶ ይንደድ

ዓለም በሞላ ትስገድ ለርሱ ክብር ይሁንለት ለንጉሱ

መውደቅ ለጠላቴ መዋረድ ለሰይጣን

መድከም ለስጋዬ መሸነፍ ለዓለም

ክብር ግን ለኢየሱስ ይሁን ለዘለዓለም

አሶር ቢነሳ በበትሩ እነ ሰናኬ ቢፎክሩ

ናቡከደነጾር ቢኮራ አንበሳው ፈርኦን ቢያጓራ

ሁሉም እንደጥላ አለፉ ከእግሩ በታች ተደፉ

እያሸነፈ እየረታ አለ ይኖራል የኛ ጌታ

መውደቅ ለጠላቴ መዋረድ ለሰይጣን

መድከም ለስጋዬ መሸነፍ ለዓለም

ክብር ግን ለኢየሱስ ይሁን ለዘለዓለም

ጌታ ከፍይበል እኛ ዝቅ ሊገን ሊከብር ሊልቅ

እርሱ ይውረሰው ሁሉን ቦታ በሁሉም ነገር ይሁን ጌታ

ይዘምርለት አፋችን ያጨብጭብለት እጃችን

ዕልልታው ይድመቅ በሆታ ይህም ያንሰዋል ለጌታ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ