በሞቱ እንድመስለው
Bemotu Endemeslew
ትራክ 7 · 4:39 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ወደ ሙታን ትንሳኤ ለመድረስ ቢሆንልኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ (8x)
የእምነት አባቶቼን ሳስባቸው በደም የደመቀ ታሪካቸው
በወህኒ በስራት በመከራ በጉድጓድ በዋሻ በተራራ
የተቅበዘበዙ እሳት የበላቸው ለቃልኪዳን እንጂ መቼ ለእንጀራቸው
ምሳሌነታቸው እንድከተል አርገኝ በልክስክስ ቦታ ከመሞት ጠብቀኝ
አዝማች · Chorus
ወደ ሙታን ትንሳኤ ለመድረስ ቢሆንልኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ (8x)
ሰው ሁሉ ቢክድህ እኔ አልክድህ ካንተ ይልቅ እራሴን አልወድ
ብዬ ስመጻደቅ ስቀናጣ ያቺ ፈታኝ ሰዐት ስትመጣ
ኢየሱስን አላውቅም ብዬ እንዳልራገም አፌን ጠብቅልኝ ዛሬም ቢሆን ነገ
መስቀሌን አግዘኝ ብለህ ስትለምነኝ የዓለምን እሳት ከመሞቅ አድነኝ
አዝማች · Chorus
ወደ ሙታን ትንሳኤ ለመድረስ ቢሆንልኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
በሞቱ እንድመስለው : እመኛለሁ (8x)
የአንድ ሰሞን ወሬ ክብር ዝና መስቀል ያልፈተነው ጉብዝና
የአንድ ሰሞን ሙቀት ሀሌሉያ አይሆንም መለኪያ መታወቂያ
ካላለፍኩኝ በቀር ያቺን ቀውጢ ሰዓት አንተን አስከብሬ በመከራ እሳት
ፍጻሜዬ እንዲያምር ጉዞ እንዲሰምርልኝ ጌታ ሆይ ፈሪ ነኝ እምነት ጨምርልኝ
አዝማች · Chorus
ወደ ሙታን ትንሳኤ ለመድረስ ቢሆንልኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
በሞቱ እንድመስለው እመኛለሁ (8x)
ደካማው ስጋዬ ሲስገበገብ የዓለም ነገር እንደው አይጠገብ
አንዱን ስይዝ ሌላው እንዳያምረኝ ኑሮዬ በቃኝ ማለትን አስተምረኝ
ስለ ስምህ ክብር ለመንግስትህ መስፋት ሁሉን መስዋአት ላድርግ ለሚጠፉ ነፍሳት
ገንዘቤ ገንዘብህ ቤቴም የአንተ ቤት እንድሞት አድርገኝ የጻድቃንን ሞት
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ