ማንን እንደጣለ ይጥልሃል
Manen Endetale Yetelehal
ትራክ 4 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ማንን እንደጣለ ይጥልሀል
ማንን እንደተወ ይተውሀል
ጌታ አንተን እጅግ ይወድሀል
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁሉን ያደርግ ዘንድ ቻይ ነውና አምላኬ
እጠብቀዋለው ፊቱ ተንበርክኬ
አዋጅን በአዋጅ ሲሽር ሰምቻለው
እሳትን በእሳት ሲያጠፋ አይቻለው
አዝማች · Chorus
ማንን እንደጣለ ይጥልሀል
ማንን እንደተወ ይተውሀል
ጌታ አንተን እጅግ ይወድሀል
ቁጥር 2 · Verse 2
የቆሸሸን ታሪክ ከማህደር ያወጣል
ልብን ብቻ አይደለም ስምን ይለውጣል
በሰው የተናቁ መንገድ የተጣሉ
ብዙዎች ናቸው በርሱ አንቱ የተባሉ
አዝማች · Chorus
ማንን እንደጣለ ይጥልሀል
ማንን እንደተወ ይተውሀል
ጌታ አንተን እጅግ ይወድሀል
ቁጥር 3 · Verse 3
ለሰይጣን ሹክሹክታ ጆሮህን አትክፈት
ጌታ ያነሳሀል ዛሬ ካለህበት
ሁሉም ነገር አልፎ ታሪክ ታወራለህ
ስለክብሩ ቆመህ ትመሰክራለህ
አዝማች · Chorus
ማንን እንደጣለ ይጥልሀል
ማንን እንደተወ ይተውሀል
ጌታ አንተን እጅግ ይወድሀል
ቁጥር 4 · Verse 4
እንደ አውራ ጎዳና ሆነህ መራገጫ
ሁሉም ለምኞቱ አርጐህ መወጣጫ
እንደወደክ አትቀር እንደተረሳህ
ጨው ነው የምትሆነው ጌታ ሲያነሳህ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ