Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እለምንሃለሁ አንድ ነገር

Elemenehalehu And Neger

ትራክ 2 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሳር ብንሰራ ባገዳ

ተቃጥሎብን እንዳንጎዳ

የሚያነጥር እሳት ሲመጣ

ማነው ተፈትኖ ሚወጣ

ጌታ ሆይ እኔ ምለምንህ (እለምንሀለው) አንድ ነገር

የኖርኩትን ኑሮ እንድናገር

የተናገርኩትን እንድኖር

እርዳኝ በዚህ ዘመን (፪x)

በጨለማ የተሰወረ

በማስመሰል ኑሮ የኖረ

ወደ ብርሀን ታወጣለህ

ለሁሉም እንደስራው ትሰጣለህ

ጌታ ሆይ እኔ ምለምንህ (እለምንሀለው) አንድ ነገር

የኖርኩትን ኑሮ እንድናገር

የተናገርኩትን እንድኖር

እርዳኝ በዚህ ዘመን (፪x)

አንዳንዱ ለደሞዝ ይሰብካል

ሌላኛው ለጥቅም ያመልካል

ታዲያ ማነው አንተን ፈላጊ

የተናገረውን አድራጊ

ጌታ ሆይ እኔ ምለምንህ (እለምንሀለው) አንድ ነገር

የኖርኩትን ኑሮ እንድናገር

የተናገርኩትን እንድኖር

እርዳኝ በዚህ ዘመን (፪x)

ባፌ ብዙ ፍቅርን ስገልጥ

ወንድሜን በነገር ስረግጥ

ቃል አባይ ሆኜ እንዳልገኝ

ጌታ ሆይ ከሀሰት ጠብቀኝ

ጌታ ሆይ እኔ ምለምንህ (እለምንሀለው) አንድ ነገር

የኖርኩትን ኑሮ እንድናገር

የተናገርኩትን እንድኖር

እርዳኝ በዚህ ዘመን (፪x)

በጓዳም ይሁን በጎዳና

ነውር የሌለባት ህሊና

በእግዚአብሄርና በሰው ፊት

እንድራመድ እርዳኝ በእውነት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ