ጌታ ሆይ አንድ ሰው ስጠን
Gieta Hoy And Sew Seten
ትራክ 6 · 6:56 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ (፪x) አንድ ሰው ስጠን
የእግዚአብሔር ቅባት ያለበት
ቁጥር 1 · Verse 1
ቢባርክ የሚደርስለት ቢረግም የሚሆንለት
ቢገስፅ የምንሰማው ቢቆጣን የምንፈራው
ስንተኛ የሚያነቃን ስንሮጥ የሚያቆመን
ጌታ ሆይ አንድ ሰው ስጠን (፪x)
ፍቅርን ተቀብሎ የሚሰጥ የፍቅር መጋቢ
ሀብታም ደሀ ብርቱ ደካማ ሁሉንም ሰብሳቢ
በፍቅር በርህራሄ በትዕግስት መንጋህን ሚመራ
የቆሰለ ፈዋሽ መድኃኒት ደራሽ በመከራ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ (፪x) አንድ ሰው ስጠን
የእግዚአብሔር ቅባት ያለበት
ቁጥር 2 · Verse 2
ቢረግምም የሚደርስለት ቢባርክ የሚሆንለት
ቢከፋን የምናዋየው ቢደክመን የምናርፍበት
ብንቆስል የሚፈውሰን ብናዝን የሚያፅናናን
ጌታ ሆይ አንድ ሰው ስጠን (፪x)
ጩኸት አብዝተናል ውድድር እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ
ሁላችንም እኩል ሆነናል የለም መደማመጥ
እረፉ የሚለን ተቆጪ እንደምን እንጣ
ጌታሆይ እባክህ አንድ ሰው በቅባትህ አውጣ
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ (፪x) አንድ ሰው ስጠን
የእግዚአብሔር ቅባት ያለበት
ቁጥር 3 · Verse 3
ቢባርክ የሚደርስለት ቢረግምም የሚሆንለት
ስንበድል የሚገስፀን ስንስት የሚመልሰን
ስንጣላ የሚያስታርቀን ስንበተን ሚሰበስበን
ጌታ ሆይ አንድ ሰው ስጠን (፪x)
ቃሉ ከምድር ጠብ የማይል ቀንዱ ዘይት የሞላ
ለተገፉ ድሆች ተሟጋች ጉቦ የማይበላ
ለእውነት ኖሮ ለእውነት የሚሞት በዚህ ክፉ ዘመን
ነገስታት ሲያጠፉ ሀይ የሚል ሳሙኤልን ስጠን
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ (፪x) አንድ ሰው ስጠን
የእግዚአብሔር ቅባት ያለበት
ቁጥር 4 · Verse 4
ቢባርክ የሚደርስለት ቢረግምም የሚሆንለት
ስንፈራ ሚያደፋፍረን ስንጨነቅ አይዞ የሚለን
ስንገፋ ሚሟገትልን ስንናቅ የሚቆምልን
ጌታ ሆይ አንድ ሰው ስጠን (፪x)
ቅድስት ከተማ ቅጥሯ ፈርሶ መቅደሱ ሲቃጠል
በንጉስ ጮማ በወይን ጠጅ የማይቀማጠል
ህዝብህን የሚያነሳሳ ቅጥሩን ለመጠገን
ክብሩን ስለ ክብርህ የተወ ነህምያን ስጠን
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ (፪x) አንድ ሰው ስጠን
የእግዚአብሔር ቅባት ያለበት
ቁጥር 5 · Verse 5
ቢባርክ የሚደርስለት ቢረግምም የሚሆንለት
ስንተኛ የሚያነቃን ስንሰንፍ የሚያተጋን
ስንወድቅ የሚያነሳን ስንደክም የሚያበረታን
ጌታ ሆይ አንድ ሰው ስጠን (፪x)
ሙሴ ወይ ኢያሱ ኤልያስ ዼጥሮስ ቢሆን ዻውሎስ
ብቻ ጌታችን ሆይ አንድ ሰው አስነሳ በመንፈስ
አደባባይ ሞልቶ መፍሰሱ ምን አለው ቁም ነገር
አንተ የቀባኸው አንድ ሰው ይበቃል ለሀገር
አዝማች · Chorus
ጌታ ሆይ (፪x) አንድ ሰው ስጠን
የእግዚአብሔር ቅባት ያለበት
ቁጥር 6 · Verse 6
ቢባርክ የሚደርስለት ቢረግምም የሚሆንለት
ጓዳችንን የምናሳየው ሚስጥራችንን የምናዋየው
በፍቅር የሚገስፀን በትዕግስት የሚሸከመን
ጌታ ሆይ አንድ ሰው ስጠን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ