ጌታቸው በመጣ ጊዜ
Gietachew Bemeta Gizie
ትራክ 9 · 5:48 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው
እነዚያ ባሮች ብጹኁን ናቸው (፪x)
አስቀምጦ ያገለግላቸዋል በማዕዱ
እኔንም አርገኝ ከእነርሱ እንደ አንዱ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቀጠሮ አፍራሽ የጊዜ ሌባ መምሸቱን አውቆ ቤቱ ማይገባ
ከዘመን ኋላ ኋላ ተጎታች የሁሉም ጭራ ከሁሉም በታች
ከቶ የማይገባኝ የህይወት ነገር እንዳልሆንብህ እንዳትቸገር
እግሬ መራመድ እንዳያቅተው የሩቁን እንዳይ አይኔን ክፈተው
አዝማች · Chorus
ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው
እነዚያ ባሮች ብጹኁን ናቸው (፪x)
አስቀምጦ ያገለግላቸዋል በማዕዱ
እኔንም አርገኝ ከእነርሱ እንደ አንዱ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዓለም ስትከፋ ዘመን ሲጨልም ምርምር በዝቶ እምነት ሲደክም
ፈጣሪን መፍራት ከምድር ሲጠፋ ፍጥረት ሲደገፍ በራሱ ተስፋ
ቆይ ይደረሳል ማለት ይበቃል ነገን መኖሬን እግዚአብሄር ያውቃል
ይልቅ ልነሳ ልክፈተው ደጁን መለከት ልንፋ ልንገር አዋጁን
አዝማች · Chorus
ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው
እነዚያ ባሮች ብጹኁን ናቸው (፪x)
አስቀምጦ ያገለግላቸዋል በማዕዱ
እኔንም አርገኝ ከእነርሱ እንደ አንዱ
ቁጥር 3 · Verse 3
የመምጫውን ቀን ከቶ ማን ያውቃል ጠብቁኝ ብሎ ያስጠነቅቃል
የድል መለከት ሲነፋ ከላይ አንዷ በወፍጮ ሌላው በእርሻው ላይ
ምጥ እርጉዝን ሴት እንደሚይዛት ድንገት ይሆናል የጌታ መምጣት
በውጭ ጨለማ መጣል ይመጣል በተጠንቀቅ ግን መቆም ያዋጣል
አዝማች · Chorus
ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው
እነዚያ ባሮች ብጹኁን ናቸው (፪x)
አስቀምጦ ያገለግላቸዋል በማዕዱ
እኔንም አርገኝ ከእነርሱ እንደ አንዱ
ቁጥር 4 · Verse 4
የማጽናኛ ቃል ለደከሙቱ የጥሪ ደወል ውጪ ላሉቱ
በህይወት ማእበል ለሚንገላቱ የጸሎት ድጋፍ እንዲበረቱ
አልነጋ ላለው ለጨለመበት መቆም እንድችል በፈረሰበት
ባርከኝ በብዙ አታሳንሰኝ እየቆራረጥክ ለብዙ አድርሰኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ