አንድ ነገር የምፈራው
And Neger Yemeferaw
2011 · ትራክ 12 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈራው
አንተ ዝም ስትለኝ ነው (፪x)
አንድ ነገር በሕይወቴ የምሰጋው
አንተ ዝም ስትለኝ ነው (፪x)
እባክህ ተናገረኝ ኢየሱስ ዝም አትበለኝ
ቁጥር 1 · Verse 1
ሁሉን ወደምትችል ወደአንተ እጮሃለሁ
ልትረዳኝ እንደምትችል ይህንን አውቃለሁ
በወደድከው መንገድ ጌታ ተናገረኝ
ብቻ አንድ ነገር ኢየሱስ ዝም አትበለኝ
ብቻ አንድ ነገር አባ ዝም አትበለኝ
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈራው
አንተ ዝም ስትለኝ ነው (፪x)
አንድ ነገር በሕይወቴ የምሰጋው
አንተ ዝም ስትለኝ ነው (፪x)
እባክህ ተናገረኝ ኢየሱስ ዝም አትበለኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሙግቴ ከአንተ ጋር መሆኑን ስታውቀው
ለምን ዝም እንዳልከኝ ያልገባኝ ሚስጥር ነው
ተናገረኝ ጌታ ያየኸው ጉድለቴን
አንተ ዝም ካልክማ ሌላ ማነው ያለኝ
አንተ ዝም ካልክማ ሌላ ማንም የለኝ
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈራው
አንተ ዝም ስትለኝ ነው (፪x)
አንድ ነገር በሕይወቴ የምሰጋው
አንተ ዝም ስትለኝ ነው (፪x)
እባክህ ተናገረኝ ኢየሱስ ዝም አትበለኝ
ቁጥር 3 · Verse 3
አንተ ዝም ባልክበት በካህኑ ኤሊ ዘመን
ድል አይታወቅም ሁሌ መሸነፍ ነው
እስከ ሲዖል ድረስ ነፍስን ያወርዳታል
የአንተ ዝምታ ነፍሴን ያሰጋታል (፪x)
አዝማች · Chorus
አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈራው
አንተ ዝም ስትለኝ ነው (፪x)
አንድ ነገር በሕይወቴ የምሰጋው
አንተ ዝም ስትለኝ ነው (፪x)
እባክህ ተናገረኝ ኢየሱስ ዝም አትበለኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
መልሰህ መላልሰህ ብትናገረኝም
ማስተዋል ቢያቅተኝ ተው አትሰልቸኝ
በአባትነት ፍቅርህ በልምጭ ሾጥ አርገኝ
ዝም ካልከኝማ አባ ዋጋም የለኝ
ዝም ካልከኝማ ኢየሱስ ዋጋም የለኝ
ቁጥር 5 · Verse 5
አንድ ነገር በሕይወቴ የምረካው
ቁጥር 6 · Verse 6
አንተ ስትናገረኝ ነው (፪x)
አንድ ነገር በሕይወቴ የምፈታው
አንተ ስትናገረኝ ነው (፪x)
እባክህ ተናገረኝ እለመልማለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ