በዘለዓለም ዙፋን ላይ
Bezelealem Zufan Lay
2011 · ትራክ 7 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
በዘለዓለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የታለ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ዘንዶውን ገጥመህ ያሸነፍክ ጌታ
በሃይል በስልጣን የምትበረታ
ጽኑ ሃያላንን ሁሉ ያሸነፍክ
የሃያል ሃያል ኢየሱስ ብርቱ ነህ
አዝማች · Chorus
በዘለዓለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የታለ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ቁጥር 2 · Verse 2
ሰማይ ምድርን በስልጣንህ ቃል
ፍጥረት እስኪደነቅ ሰርተሃቸዋል
ስላልተገኘልህ ከቶ ለአንተ አቻ
ስምህ ገነነ እስከምድር ዳርቻ
አዝማች · Chorus
በዘለዓለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የታለ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሃይልህ ከሃያላን ሁሉ ይበልጣል
ውሃን እንደግምብ ቀጥ አድርጐ ያቆማል
ከአጥፊዎችም እጅ ክንድህ ያስጥላል
የይሁዳ አምበሳ ማን ይመስልሃል
አዝማች · Chorus
በዘለዓለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የታለ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሃይልህን ሳያውቁ የተነሱብህ
አስከትተው ጦር የዘመቱብህ
ክንድህ ገጥሟቸው ተሸንፈዋል
ስማቸው ጠፍቶ አንተ ነግሰሃል
አዝማች · Chorus
በዘለዓለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የታለ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ
ቁጥር 5 · Verse 5
ሰማይ ምድርን በስልጣንህ ቃል
ፍጥረት እስኪደነቅ ሰርተሃቸዋል
ስላልተገኘልህ ከቶ ለአንተ አቻ
ስምህ ገነነ እስከምድር ዳርቻ
አዝማች · Chorus
በዘለዓለም ዙፋን ላይ ተቀምጠህ ያለህ
በሰማይም በምድርም ሙሉ ስልጣን ያለህ
ዙፋንህ ተነቃንቆ ተገርስሶ የታለ
እግዚአብሔር እግዚአብሔር ነህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ