መድሃኒቴ
Medhanitie
2011 · ትራክ 1 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለእኔ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ስሙን ላክብረው
ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ሰው ወዳጁን ቢወድ ለጥቂቱ ነው
ጥቅሙም ሲቀር ፍቅሩም ቀሪ ነው
እኔ ግን ጠላትህ ሳለሁ ወደድከኝ
በዘለዓለም ፍቅርህ ኢየሱስ አሰብከኝ
አዝማች · Chorus
መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለእኔ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ስሙን ላክብረው
ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
መንገድ ላይ ወድቄ ጠላቴ አቁስሎኝ
ማንም አልነበረም ከውድቀት ያነሳኝ
ዘይትን አፍስሦ ቁስሎቼን የቀባኝ
እንደ ኢየሱሴ የለኝም አዳኝ
አዝማች · Chorus
መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለእኔ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ስሙን ላክብረው
ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ድካም ችግሬን የምትሸፍንልኝ
ምርኩዝ ድጋፌም ጋሻም የሆንከኝ
ከእናት ከአባቴም የምትበልጥብኝ
መድሃኔቴ ሆይ ከፍ በልልኝ
አዝማች · Chorus
መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው ለእኔ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ስሙን ላክብረው
ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
አንድ ሁለት ብዬ ቁጥር ብሰጠው
ጌታ ውለታህ ከልክ በላይ ነው
እንደ እኔ ውለታው የበዛባችሁ
ቅኔን ተቀኙለት እልል ብላችሁ
ቁጥር 5 · Verse 5
መድሃኒቴ ብዙ ብዙ ነው (ብዙ ብዙ ነው)
ቁጥር 6 · Verse 6
ለእኔ ያረገው (ያረገው)
እንደገና ስሙን ላክብረው (ስሙን ላክብረው)
ውለታው ለእኔ ብዙ ነው (ለእኔ ብዙ ነው) (፪x)
ዕልልታ!
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ