የማልጠግበው
Yemaltegbew
2011 · ትራክ 9 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ከሞት የበረታ ፍቅሩ አሽነፈኝ
ነፍስም አልቀረልኝ ወድጄዋለሁኝ
ሰዎች ሌላም ቢሉም ለእኔ ግን ፍቅር ነው
ኢየሱስ ኢየሱስ ብዬ የማልጠግበው
ቁጥር 2 · Verse 2
የማልጠግበው እኔስ የማልጠግበው
ቁጥር 3 · Verse 3
የማልጠግበው እኔስ ኢየሱሴን ነው (፪x)
በመልካምነቱ ደስታን አጠገበኝ (፪x)
ባርኮቱ በሞላው ድንኳኑ ያኖረኝ (፪x)
ሥጋት ቀርቶልኛል ተደላድያለሁ (፪x)
የእግዚአብሔር ልጅ ነው ከእኔ ጋራ ያለው (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከሰው ሁሉ ልዩ እርሱን የሚያደርገው
ቁጥር 5 · Verse 5
ፍቅሩ ወረት አያውቅ ዘለዓለማዊ ነው (፪x)
የሚከታተለኝ በሄድኩበት ቦታ (፪x)
ዐይኖቹ ዐይነሱም ከእኔ ላይ ለአንድ አፍታ (፪x)
የገባኝ ይሄ ነው እንዲሁ ወዶኛል (፪x)
ፍቅሩም ከማር ይልቅ እጅግ ይጣፍጣል (፪x)
አዝማች · Chorus
ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅሩ አጥግቦኛል
እኔስ ሌላ አልሻም ኢየሱስ ይበቃኛል (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ያስደንቀኝ ጀመረ እየዋለ እያደር (፪x)
በእኔ ላይ የበዛውን ምህረቱን ስቆጥር (፪x)
ፍቅርና ምህረቱ ከቶ ገደብ የለው (፪x)
ይህን ኢየሱሴን ነፍሴ ወደደችው (፪x)
አዝማች · Chorus
ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅሩ አጥግቦኛል
እኔስ ሌላ አልሻም ኢየሱስ ይበቃኛል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ