ከልቤ የፈለቀ
Kelebie Yefeleqe
2011 · ትራክ 8 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እያስገረመኝ አሃሃሃ እያስደነቀኝ አሃሃሃ
የአንተ ምህረት አሃሃሃ ቃላት አሳጣኝ አሃሃሃ
መሽቶ እስኪነጋ አሃሃሃ መቁጠር እስከሚያቅት አሃሃሃ
የአንተን ደግነት አሃሃሃ እንከን የሌለበት አሃሃሃ
አዝማች · Chorus
ተባረክ ተባረክ ተባረክ ወዳጄ
ምሥጋና ነው ያለኝ ይኸውና በእጄ/ከእጄ
ከልቤ የፈለቀ የምሥጋና መስዋዕት
እሰዋልሃለሁ አሽተተው የእኔ አባት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ተፈጸመ ብሎ ነግሮኛል ጌታዬ አሃሃሃ
በመስቀል ላይ ውሎ አሃሃሃ ተከፍሎ እዳዬ አሃሃሃ
እንዲህ እንዲያ እያለ ማነው የሚከሰኝ አሃሃሃ
ብሩክ የእግዚአብሔር ልጅ አሃሃሃ ጠበቃ ስላለኝ አሃሃሃ
አዝማች · Chorus
ተባረክ ተባረክ ተባረክ ወዳጄ
ምሥጋና ነው ያለኝ ይኸውና በእጄ/ከእጄ
ከልቤ የፈለቀ የምሥጋና መስዋዕት
እሰዋልሃለሁ አሽተተው የእኔ አባት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እስቲ ልነሳና አሃሃሃ ወደቤቴ ልውጣ አሃሃሃ
ለያዕቆብ አምላክ አሃሃሃ መስዋዕቴን ልሰዋ አሃሃሃ
እንደ ስፍሪዳ አሃሃሃ ያማረ ምሥጋና አሃሃሃ
ላምጣ ልሰዋልህ አሃሃሃ ደግ አምላክ ነህና አሃሃሃ
አዝማች · Chorus
ተባረክ ተባረክ ተባረክ ወዳጄ
ምሥጋና ነው ያለኝ ይኸውና በእጄ/ከእጄ
ከልቤ የፈለቀ የምሥጋና መስዋዕት
እሰዋልሃለሁ አሽተተው የእኔ አባት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ