በአማልክቶች በካከል
Beamalektoch Mekakel
2011 · ትራክ 11 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ብዙዎች ተነሱ ሃያላን የተባሉ
በጦር በሰልፍ ብዛት ስማቸውን ያስጠሩ
አልኖሩም አለፉ ሞት አሸነፋቸው
ሃያል አንተ ብቻ እያሸነፍካቸው
አዝማች · Chorus
በአምልክቶች መካከል እንደአንተ የለም
ንጉሥ ሆይ ንገሥ ዘለዓለም (፪x)
በአምልክቶች መካከል እንደአንተ የለም
ጌታ ሆይ ክበር ዘለዓለም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ታቦቱንም ወሰዱና አቋቆሙት ከዳጐን ጋር
መቼ ችሎት ፊቱ ቆመ
ያማረው ዳጐን ተሰባበረ (፪x)
አዝማች · Chorus
በአምልክቶች መካከል እንደአንተ የለም
ንጉሥ ሆይ ንገሥ ዘለዓለም (፪x)
በአምልክቶች መካከል እንደአንተ የለም
ጌታ ሆይ ክበር ዘለዓለም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ይህ ታላቅ አምላክ ይዤ
ለማይሰማ አምላክ አልሰግድም
በእቶኑ እሳት ብጣል እንኳን
ስለሚወደኝ ይደርስልኛል
ስለሚወደኝ ፈጥኖ ይመጣል
አዝማች · Chorus
በአምልክቶች መካከል እንደአንተ የለም
ንጉሥ ሆይ ንገሥ ዘለዓለም (፪x)
በአምልክቶች መካከል እንደአንተ የለም
ጌታ ሆይ ክበር ዘለዓለም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከባዖል ነቢያት ጋራ ሲወዳደር ተዐምር ሰራ
ሰምቶ በእሳት መለሰ
ከእነሱ አምላክ የእኔ በለጠ
ከእነሱ አምላክ ኢየሱስ በለጠ
አዝማች · Chorus
በአምልክቶች መካከል እንደአንተ የለም
ንጉሥ ሆይ ንገሥ ዘለዓለም (፪x)
በአምልክቶች መካከል እንደአንተ የለም
ጌታ ሆይ ክበር ዘለዓለም (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ብዙዎች ተነሱ ሃያላን የተባሉ
በጦር በሰልፍ ብዛት ስማቸውን ያስጠሩ
አልኖሩም አለፉ ሞት አሸነፋቸው
ሃያል አንተ ብቻ እያሸነፍካቸው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ