ተመስገን
Temesgen
2011 · ትራክ 10 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መከራን ባየሁበት ምድር
በገፉኝ ሰዎች ልከበር
ታሪኬን ከገለበጥከው
ልቤን ደስ ካሰኘኸው
ምሥጋናዬን ይኸው በፊትህ
እንዳከበርከኝ ላከብርህ
ያለኝም ይኸው ነውና
አንተው ከሰጠኸኝ ሌላ አሃሃ
አንተው ከሰጠኸኝ ሌላ
አዝማች · Chorus
ተመስገን ጌታ ተመስገን
ተመስገን ተመስገን (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በምሽት በሬ ሲንኳኳ
መች መሰለኝ የምትመጣ
ለካ ከሩቅ ተመልክተህ
አስተዳዳሬ የአላማረህ
አንተው ነህ የተጠጋኸኝ
አስፈሪውን ሌት ያሳለፍከኝ
ከብሬን ከደጄ አፍስሰህ
ጠረኔን ለወጥክ አጣፍጠህ አህህ
ጠረኔን ለወጥክ አጣፍጠህ
አዝማች · Chorus
ተመስገን ጌታ ተመስገን
ተመስገን ተመስገን (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ምሥጋናዬን ከወደድከው
ስሰዋውም ካሸተትከው
ከቃዬል መስዋዕት ካስበለጥከው
ለአንተ ስሰዋ ውላለሁ
ቀጥ ብሎ ወደላይ ይውጣ
አርጐ በፊትህ ጌታ
ደስ የሚያሰኝህ ምሥጋና
ይሽተት ማደሪያህ ይግባና
አሜን ይሽተት ማደሪያህ ይግባና
አዝማች · Chorus
ተመስገን ጌታ ተመስገን
ተመስገን ተመስገን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ