አንድ ወዳጅ
And Wedaj
2006 · ትራክ 2 · 6:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንድ ወዳጅ (፪x) አለኝ
ለእኔ የሞተልኝ (፬x)
ቅጣቴን የተቀጣህልኝ
አበሳዬን ከእኔ ወሰድክልኝ (፪x)
ጌታ ተባረክልኝ
ኢየሱስ ተባረክልኝ
ጌታ ተባረክልኝ (፪x)
ሙግቴን ተሟግቶ አሸንፎልኛል
ጠላቴ እንዳይከሰኝ ነጻ ነህ ብሎኛል
ይህን ወዳጄን ወዳጄ ነህ ያልኩት
ከማንም አብልጬ በልቤ የሾምኩት
አዝማች · Chorus
ለእኔ መልካም በማድረግ የታወቀው
መልካም በማድረግ የታወቀው
ለእኔ መልካም በማሰብ የታወቀው
መልካም በማሰብ የታወቀው
እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው (፪x)
እርሱ ጌታዬ ነው ጌታዬ ነው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በምክሩ ግሩም ነው ነፍስን ይመልሳል
ከወዳጅ አብልጦ ወደ ልብ ይጠጋል
ደብቆ የያዘኝ እንዳልሆን የሌላ
የቅርቤ የምለው ማነው ከእርሱ ሌላ
አዝማች · Chorus
ለእኔ መልካም በማድረግ የታወቀው
መልካም በማድረግ የታወቀው
ለእኔ መልካም በማሰብ የታወቀው
መልካም በማሰብ የታወቀው
እርሱ እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር ነው (፪x)
እርሱ ጌታዬ ነው ጌታዬ ነው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ