ምክርህ ሲፀና
Mekereh Sitsena
2006 · ትራክ 13 · 4:42 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምክርህ ሲሰራ አይቼ ተደስቻለሁ
ማይከለከል ሃሳብህ አውቄዋለሁ
ድንቅህን አይቼ ብገረም ቆምኩኝ ላመልክህ
በሰው ሁሉ ፊት ተገልጧል አደራረግህ
አዝማች · Chorus
ተባረክ ከዚህ ሌላ ምን እላለሁ
ጌታዬ አንተ ነህ አውቄያለሁ
ዘመኔን ከአንተ ጋር እንድኖር ጌታ
በቃልህ/በምክርህ ደገፍከኝ እንዳልረታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አንተን አምኜ ወደፊት እራመዳለሁ
ወሬ ሰምቼ ኋላዬን መቼ አያለሁ
ዘለዓለሜ በእጅህ ነው ልቤ እንዳይሰጋ
የምታመንህ ጌታዬ አለህ ከእኔ ጋር
አዝማች · Chorus
ተባረክ ከዚህ ሌላ ምን እላለሁ
ጌታዬ አንተ ነህ አውቄያለሁ
ዘመኔን ከአንተ ጋር እንድኖር ጌታ
በቃልህ/በምክርህ ደገፍከኝ እንዳልረታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የሰው ዓይን የለህ እንደሰው መቼ ታያለህ
ጆሮህስ እንደሰማቸው መች ትፈርዳለህ
መንገዱ ይሄ ነው ብሎ ሚመራህ የለም
በምክርህ ግሩም ትክክል ጻድቅ አምላክ ነህ
አዝማች · Chorus
ተባረክ ከዚህ ሌላ ምን እላለሁ
ጌታዬ አንተ ነህ አውቄያለሁ
ዘመኔን ከአንተ ጋር እንድኖር ጌታ
በቃልህ/በምክርህ ደገፍከኝ እንዳልረታ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ለዘሪ ዘርን የምትሰጥ ፍሬ እንዲበላ
ከሕይወት እንዳይጐድል ሞቶ የኋላ ኋላ
ለእኔም ቃልህን ሰጥተኸኛል ምን አስባለሁ
ተስፋ ቢስ ሆኜ አልቀረሁም አከብርሃለሁ
አዝማች · Chorus
ተባረክ ከዚህ ሌላ ምን እላለሁ
ጌታዬ አንተ ነህ አውቄያለሁ
ዘመኔን ከአንተ ጋር እንድኖር ጌታ
በቃልህ/በምክርህ ደገፍከኝ እንዳልረታ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ