የሚያውቅልኝ ጌታ
Yemiyawqelegn Gieta
2006 · ትራክ 3 · 4:51 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሚያውቅልኝ ጌታ ያውቅልኛልና
ሰው አልደገፍም ይሰበራልና
ዛሬ ታይቶ ነገ በሚጠፋው ነገር
አዝማች · Chorus
ልቤን በዚያ አልጥልም አለልኝ እግዚአብሔር (፪x)
አለልኝ እግዚአብሔር (፬x)
አለልኝ አለልኝ የሚያስብልኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የበላይ ነህ ጌታ የሁሉ በላይ
እኩያ የሌለህ በምድር በሰማይ (፪x)
አምላክ አለኝና ሁሉን በእጁ የያዘ
ሥሙም ድንቅ መካር ኃያል የተባለ
ሰማይና ምድርን በቃሉ እንዳፀና
እርሱን ባይሁ ጊዜ እኔም ልቤ ፀና (፭x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ግራ አይገባኝም ነገን አስቤ ለወደፊቱ
የታመንኩበት ሁሉ በእጁ ነው ሁሉ በደጁ
የእንቆቅልሽ ሁሉ መፍቻ ቁልፍ ያለው
የይሁዳ አንበሳ ከእኔ ጋራ ነው
አዝማች · Chorus
እንዳለው ነው እንደ ቃሉ
ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ
እንዳለው ነው (እንዳለው ነው)
እንደ ቃሉ (እንደ ቃሉ)
ሁሉ በእጁ (ሁሉ በእጁ)
ሁሉ በደጁ (ሁሉ በደጁ) (፪x)
የበላይ ነህ ጌታ የሁሉ በላይ
እኩያ የሌለህ በምድር በሰማይ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ