Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ተዓምር ነው

Teamer New

2006 · ትራክ 6 · 4:58 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ስለደህንነቴ/ስለመጠራቴ ዘምሬ ሳልጨርስ

ወደ ሌላ አላልፍም ጐርፍ . (1) . ቢደርስ

በክብር ወደላይ ያረገውን ንጉሥ

ደስታዬ ልክ የለው እርሱን ሳሞጋግስ (፪x)

እርሱን ሳሞጋግስ (፪x) ፣ ጌታን ሳሞጋግስ (፪x)

እርሱን ሳሞጋግስ (፪x) ፣ ጌታን ሳሞጋግስ (፪x)

በምሥጋና ልቁም ፊቱ በደስታ (፪x)

እግሮቼም ጸኑልኝ ቆምኩኝ በከፍታ (፪x)

መዳኔ ማምለጤ ኦሆሆ ትንግርት ሆኖብኛል (፪x)

በሚወደው ልጁ እግዚአብሔር/ጌታዬ ታርቆኛል (፪x)

ተዓምር ነው መዳኔ ለእኔ

ቆሜ ፊትህ መዘመሬ

ወደኸኝ ድኛለሁና

ተቀበል ከእኔ ምሥጋና

ከእኔ ምሥጋና ጌታ ፤ ከእኔ ምሥጋና

ከእኔ አምልኮ ፤ ከእኔ አምልኮ

ከእኔ ዝማሬ ፤ ከእኔ ዝማሬ

ከእኔ ምሥጋና ጌታ ፤ ከእኔ ምሥጋና

እኔስ ከነገሬ ድኜ መዘመሬ (፪x)

ከሁሉም ሚበልጠው መዳኔ ነው ክብሬ (፪x)

ሰው ሆነህ ከሰማይ የወረድከው ጌታ (፪x)

ሁሌ ላመስግንህ አለብኝ ውለታ (፪x)

ተዓምር ነው መዳኔ ለእኔ

ቆሜ ፊትህ መዘመሬ

ወደኸኝ ድኛለሁና

ተቀበል ከእኔ ምሥጋና

ከእኔ ምሥጋና ጌታ ፤ ከእኔ ምሥጋና

ከእኔ አምልኮ ፤ ከእኔ አምልኮ

ከእኔ ዝማሬ ፤ ከእኔ ዝማሬ

ከእኔ ምሥጋና ጌታ ፤ ከእኔ ምሥጋና

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ