ኢየሱስ ነው ጌታ
Eyesus New Gieta
2006 · ትራክ 1 · 5:08 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አምልኮ (፫x) ይለኛል
ዛሬ ደግሞ መንፈስህ በእጥፍ አግኝቶኛል
በል ዘምር (፫x) ይለኛል
የሚወደኝ ጌታ ምህረት አድርጐልኛል
ጠላት በዙሪያዬ መርዶ ሲያረዳኝ
የጌታዬ ሰላም ከላይ ሲያገኘኝ
አስባለኝ ተባረክ ጌታዬ ተባረክ
ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ (፪x)
በሰማይ በምድር አሃ አለሁ የሚል ጠፍቶ
ጀግና የተባል አሃ ሁሉ አንገቱን ደፍቶ
መጽሐፉን ወስዶ ማኅተሙን የፈታ
የይሁዳ አንበሳ ኢየሱስ ነው ጌታ
ኢየሱስ ኢየሱስ ነው ጌታ (፪x)
ጌታዬ አንተ እኮ ነህ ጌታ (፪x)
ከአንተ በላይ ጌታ ከአንተ በላይ ንጉሥ
በላዬ አልሾምኩም የናዝሬቱ ኢየሱስ
ከሥም ሁሉ በላይ ሥም ያለህ አንተ ነህ
በፍጥረት አንደበት ትመሰገናለህ
ጌታዬ ትመሰገናለህ (፪x)
ሁልጊዜ ትመሰገናለህ (፪x)
አልቅነትና ሥልጣናትን ገፎ
በአባቱ ቀኝ አለ ሁሉን አሸንፎ
የሁሉ የበላይ ሆኖ የሚገዛው
እኔ የማመልከው የጌቶች ጌታ ነው
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው (፬x)
አዝማች · Chorus
አምልኮ (፫x) ይለኛል
ዛሬ ደግሞ መንፈስህ በእጥፍ አግኝቶኛል
በል ዘምር (፫x) ይለኛል
የሚወደኝ ጌታ ምህረት አድርጐልኛል
ጠላት በዙሪያዬ መርዶ ሲያረዳኝ
የጌታዬ ሰላም ከላይ ሲያገኘኝ
አስባለኝ ተባረክ ጌታዬ ተባረክ
ተባረክ ኢየሱስ ተባረክ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ