ስላሰብከኝ
Selasebkegn
2006 · ትራክ 10 · 5:29 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እንደነጋልኝ አይቶ ጠላቴ
ከበሮውን ጥሎ ሮጠ ከፊቴ
ድሌን ለማየት አልቻለምና
ተራመድኩበት ነጋልኝና (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ በአንድ ቀን ጀንበር ታሪኬን ቀየርከው
የእኔ ጌታ ሁሉን ውብ አድርገህ አንተ ነህ የሰራኸው
ስላሰብከኝ ስለወደደከኝ ነው በቤትህ የቆምኩት
ነግቶልኝ ነው በጉባኤ መሃል ለአንተ የዘመርኩት (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ሚታመኑህን የምታኮራ
ያልተጠበቀን ድንቅ የምትሰራ
አይቼሃለሁ ስትታደገኝ
ከጠላቴ ቀስት ስታስመልጠኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ በአንድ ቀን ጀንበር ታሪኬን ቀየርከው
የእኔ ጌታ ሁሉን ውብ አድርገህ አንተ ነህ የሰራኸው
ስላሰብከኝ ስለወደደከኝ ነው በቤትህ የቆምኩት
ነግቶልኝ ነው በጉባኤ መሃል ለአንተ የዘመርኩት (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በጠዋት ማታ ጠብቀኸኛል
ከጐኔ አለህ ምን ያሰጋኛል
ጽኑ ግንቤ ነህ በጠላቴ ፊት
ከአንተ ጋር ሆኜ አላውቅም ሽንፈት (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ በአንድ ቀን ጀንበር ታሪኬን ቀየርከው
የእኔ ጌታ ሁሉን ውብ አድርገህ አንተ ነህ የሰራኸው
ስላሰብከኝ ስለወደደከኝ ነው በቤትህ የቆምኩት
ነግቶልኝ ነው በጉባኤ መሃል ለአንተ የዘመርኩት (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ