Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በለቅሶ ፈንታ

Beleqso Fenta

2006 · ትራክ 7 · 4:31 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በለቅሶ ፈንታ ደስታ

በሃዘን ምትክ እፎያታ

አደረገልኝ አምላኬ

አመልከዋለሁ ከልቤ

አመልከዋለሁ ከልቤ (፬x)

የገባሁበት ገብቶ ጌታዬ እኔን ረድቶ (፪x)

አይቻለሁኝ በዓይኔ ታሪኬ ተለውጦ

የገባሁበት ገብቶ ጌታዬ እኔን ረድቶ (፪x)

አይቻለሁኝ በዓይኔ ታሪኬ ተለውጦ

ምን ልበል ምን ልናገር

ስላረክልኝ ነገር

ምን ልበል ምን ልናገር

ከማመስገን በቀር (፪x)

በምድረበዳ መራኝ ከእጆቹ እያበላኝ (፪x)

ከአበልኝ በጐነት አንዳችም ሳያሳጣኝ (፪x)

በምድረበዳ መራኝ ከእጆቹ እያበላኝ (፪x)

ከአበልኝ በጐነት አንዳችም ሳያሳጣኝ (፪x)

ምን ልበል ምን ልናገር

ስላረክልኝ ነገር

ምን ልበል ምን ልናገር

ከማመስገን በቀር (፪x)

በቸርነቱ ነው እዚህ ያደረሰኝ

ስለወደደ ነው ወግ ማረግ ያሳየኝ

በቸርነቱ ነው እዚህ ያደረሰኝ

ስለወደደ ነው ወግ ማረግ ያሳየኝ

ተባረክ ብዬ አልረካሁም ጌታዬ (፪x) ባለውለታዬ

ከፍ በል ብዬ አልረካሁም ጌታዬ (፪x) ባለውለታዬ

ባለውለታዬ ጌታዬ ባለውለታዬ (፰x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ