አይረሳኝም
Ayresegnem
2006 · ትራክ 4 · 4:00 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እኔስ አልረሳሁም ያደረክልኝን
ከጨለማ አውጥተህ ቀን ያወጣህልኝ (፪x)
ምስኪኑን ከጉድፍ ከአመድ አንስተኸው
ከታላላቆች ጋር ስፍራ እንደሰጠኸኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አይረሳኝም የእኔ ጌታ ያረክልኝ ብዙ ውለታ
አይረሳኝም የእኔ ጌታ ስለእኔ ተንገላታህ
አይረሳኝም የእኔ ጌታ ያረክልኝ ብዙ ውለታ
አይረሳኝም የእኔ ጌታ የሆንክልኝ በጐልጐታ
ቁጥር 3 · Verse 3
መቆም መቀመጤን በፊትህ አድርገህ
ክፉ አንዳይነካኝ በዙሪያዬ ሆነህ (፪x)
የአመጽ ፈሳሽ አልፎ ቀን ወጣልኝ ለእኔ
ምክንያቱ አንተ ነህ ጌታ ለመዳኔ (፪x)
አዝማች · Chorus
የመኖሬ ምክንያቱ አንተ ነህ (፪x)
የመክበሬ ምክንያቱ አንተ ነህ (፪x)
የመቆሜ ምክንያቱ አንተ ነህ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የተቆረጠና የአለቀውን ነገሬን
ቀጥለህልኛል አይተህ መቸገሬን (፪x)
ብቻህን ያለአጋዥ የረዳኸን ጌታ
ዘምረ ያሰኘኛል በዝቶ የአንተ ውለታ (፪x)
አዝማች · Chorus
የመኖሬ ምክንያቱ አንተ ነህ (፪x)
የመክበሬ ምክንያቱ አንተ ነህ (፪x)
የመቆሜ ምክንያቱ አንተ ነህ (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ