አስታውሳለው
Astawesalew
2009 · ትራክ 12 · 5:46 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አስተምረኝ ጌታዪ ሆይ አስተካክላት ሕይወቴን
መንገዴን ሁሉ ስራመድ አንተ ከእኔ ጋራ ሁን (፪x)
ክፉና ደጉን ለይቶ ሳያውቀው
አስተምረኝ አለ ሌላው እንዳይነካው
እንካ ተረከባት ሕይወቴን አደራ
በቤትህ አንድኖር አንተን እንድፈራ
ልጅነቴን/ጉብዝናዬን ንገሥበት
እስከ እርጅና እስከ ሽበት
አዝማች · Chorus
ክበርብኝ ለየኝና
ታናሹን የአንተን ብላቴና (፪x)
መልካም አባት መቼ ይጥላል(፪x)
ቃልኪዳኑን ይጠብቃል (፪x)
ታማኝ ነው አደራ ላለው በመንገዱ ለተከተለው
ያቆመዋል በቤቱ ተክሎ ያጸናዋል ልጄ ነህ ብሎ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
አስተምረኝ ጌታዪ ሆይ አስተካክላት ሕይወቴን
መንገዴን ሁሉ ስራመድ አንተ ከእኔ ጋራ ሁን (፪x)
(አስታውሳለው) ወንድሞቼን እህቶቼን የጨቅላነት ጓደኞቼን
(አስታውሳለው) ኧረ አይጠፋም ከአዕምሮዬ የልጅነት ትዝታዬ
(አስታውሳለው) ተሰብስበን ስንዘምር አንዱ ለአንዱ ያለው ፍቅር
(አስታውሳለው) ክፋት የለ መሀላችን ያ ቅን ዘመን አቤት ሲያምር
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ