አትተወኝ
Atetewegn
2009 · ትራክ 2 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አንዳንዴ ሲከፋኝ ግራ ሲገባኝ መሄጃው ሲጠፋኝ
አምላኬ አምላኬ ብዬ እጮሃለሁ ፊትህን እፈልጋለው
ዝም አትበለኝ አትተወኝ ረዳቴ
የህመሜ ፈዋሽ አንተው ነህና መድሃኒቴ (፪x)
ምድረ በዳው ሲያንገላታኝ ሃሩሩ ሲያደክመኝ
አይዞህ ባይ ሲጠፋ የሚቆም ከጐኔ
እምባዬን አፍስሼ ተማጸንኩህ ያኔ
አንተም ደረስክልኝ አልጨከንክም በእኔ
"በመከራዬ ሰዓት የረዳኽኝ ፣ በጭንቄ ሰዓት የደረስክልኝ
ዛሬም አልሃለሁ ጌታ ሆይ አባክህን"
አዝማች · Chorus
አትተወኝ እያወከው ማንነቴን
አትተወኝ እያወከው እኔነቴን
አትተወኝ እያወከው ደካማነቴን
አትተወኝ እያወከው ውስጤን ጓዳዬን
ቁጥር 2 · Verse 2
አንዳንዴ ሲከፋኝ ግራ ሲገባኝ መሄጃው ሲጠፋኝ
አምላኬ አምላኬ ብዬ እጮሃለሁ ፊትህን እፈልጋለው
ዝም አትበለኝ አትተወኝ ረዳቴ (ረዳቴ)
የህመሜ ፈዋሽ አንተው ነህና መድሃኒቴ (ዝም አትበለኝ) (፪x)
ከአንተ ወዴት የት እሄዳለሁ ሚስጥረኛዬ ነህ
ከእስትንፋሴ ይልቅ የምትቀርበኝ ጓዴ
ዛሬስ መላው ጠፋኝ መግቢያው መውጪያው ሁሉ
ድምጽህን አሰማኝ ልሁን እንደቃልህ
"ያኔ በልጅነቴ ወራት ፣ ድምጽህን ለመስማት የነበረኝ ጉጉትና ናፍቆት
ዛሬ ግን ከውስጤ ጠፋና ወደአንተ እጮሃለሁ እባክህን (፪x)"
አዝማች · Chorus
አትተወኝ እያወከው ማንነቴን
አትተወኝ እያወከው እኔነቴን
አትተወኝ እያወከው ደካማነቴን
አትተወኝ እያወከው ውስጤን ጓዳዬን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ