አያምረኝም
Ayamregnm
2009 · ትራክ 4 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለእኔስ ሕይወት በዝቶልኛል ፣ ሕይወት በዝቶልናል
ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል
ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል (፪x)
ሰው ሁሉ እንደመሰለው ቢያወራ ብዙ ቢናገር
ለእኔ ግን የገባኝ እውነት አረገኝ በዚያው እንድቀር
ለዚህ ነው እምቢ ማለቴ ሳይገደኝ ወጣትነቴ
የዓለምን ግብዣዋን ንቄ ወገቤን ትጥቄን ማጥበቄ
አዝማች · Chorus
አያምረኝም ዛሬ ታይቶ ነገ ሚጠፋ
አያምረኝም የዓለም ክብር ጊዜያዊ ተስፋ
አያምረኝም ይሄ አይደለም ለእኔማ ክብሬ
መኖር እንጂ በእግዚአብሔር ቤት እርሱን አክብሬ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ለእኔስ ሕይወት በዝቶልኛል ፣ ሕይወት በዝቶልናል
ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል
ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል (፪x)
ትውልዱ ግራ ቢገባው የዘፈን ማዕበል ቢውጠው
ነጐደ ፍጥረት ተሰዶ ገንዘብን ዓለምን ወዶ
ቀን ሲመሽ ሌቱ ሲነጋ ለአንድ አፍታ ለቤ እንዳይሰጋ
የሰማይ ደጆች ተከፍተው የአምላኬን ውበት አያለው
አዝማች · Chorus
አያምረኝም ዛሬ ታይቶ ነገ ሚጠፋ
አያምረኝም የዓለም ክብር ጊዜያዊ ተስፋ
አያምረኝም ይሄ አይደለም ለእኔማ ክብሬ
መኖር እንጂ በእግዚአብሔር ቤት እርሱን አክብሬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ የዘለዓለም (፪x)
ሙሉ ልቤ ያረፈብህ
የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ የዘለዓለም (፪x)
ግራ ቀኙን እንዳላየው
የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ የዘለዓለም (፪x)
አንዴ ልቤን የማረከው
የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ የዘለዓለም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ