Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ወዳጄ ኢየሱስ

Wedajie Eyesus

2009 · ትራክ 11 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሄድኩበት ሁሉ ሞገስ እየሆንከኝ

ያንን ክፉ ዘመን በድል አሻገርከኝ

አሃሃሃሃ በድል አሻገርከኝ

እጄን በጅህ ይዘህ እያበረታኸኝ

ያንን ድቅድቅ ጨለማ በድንቅ አሳለፍከኝ

አሃሃሃሃ በድንቅ አሳለፍከኝ

ወዳጄ ኢየሱስ ለእኔስ ያደረከው

እጅግ ብዙ ነው (፪x)

ወዳጄ ኢየሱስ ለእኔስ ያደረከው

እጅግ ብዙ ነው (፪x)

አያልቅም ውለታህ ባወራው ብተርከው (፬x)

ለውለታህ ምላሽ ከሆነ መሥጋና (፪x)

ለስጦታህ ምላሽ ከሆነ ምሥጋና (፪x)

ልዘምር እንደገና ፤ ላምልክህ እንደገና (፬x)

አባት ሆነህ አሳድገኸኛል

ከእናት በላይ ራርተህልኛል

የቅርቤ ነህ ውዴ ለእኔ

መሳይ አጣሁልህ በዘመኔ (፪x)

ወዳጄ ኢየሱስ ለእኔስ ያደረከው

እጅግ ብዙ ነው (፪x)

ወዳጄ ኢየሱስ ለእኔስ ያደረከው

እጅግ ብዙ ነው (፪x)

አያልቅም ውለታህ ባወራው ብተርከው (፬x)

ወግ ማዕረጌ ክብሬ ልበልህ

ውዴ ብዬ ስላልጠገብሁህ

የልቤን የውስጤን ባይገልጸውም

እንዲያው ዝም ብዬ ልበለዉ

የፍቅርህን ልኩን ባልገልጸዉ

እንዲያው ዝም ብዬ ልበለዉ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ