ወደድከኝ
Wededkegn
2009 · ትራክ 3 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ወደድከኝ(፫x) እንዲያው ወደድከኝ
ወደድከኝ(፫x) የፍቅር ነህ እንዲያው ወደድከኝ
ቁጥር 2 · Verse 2
ታዛዥ አልነበርኩም አመጸና እንቢተኛ
እንደልቤ ምኖር ዓለም ወዳድ ዓለመኛ
ፍቅርህ ሰው አደረገኝ ወደውስጤ ዘልቆ ገባ
ከቅዱሳን ጋራ ሰበሰበኝ እንድልህ አባ
አባ ልበል ከወደድከኝ ፣ አባ ልበል ከመረጥከኝ
አባ ልበል በቸርነትህ ፣ አባ ልበል ከደገፍከኝ
አባ ልበል ልስገድልህ ፣ አባ ልበል ልቀኝልህ
አባ ልበል እንዳየህልኝ ፣ አባ ልበል ልኑርልህ
አዝማች · Chorus
አባብዬ (፪x) አንተ እኮ ነህ እድል ፈንታዬ
አብትዬ (፪x) አንተ እኮ ነህ እድል ፈንታዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
ወደድከኝ(፫x) እንዲያው ወደድከኝ
ወደድከኝ(፫x) የፍቅር ነህ እንዲያው ወደድከኝ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሰዎች የናቁትን የገፉትን የረሱትን ሰው
ሰው አይሆንም ብለው የተዉትን አንተ ታደከው
ዛሬ በአደባባይ ይዘምራል ተቀብቶ
የአለፈው ታሪኩ እንዳለፈ ዉሃ ተረስቶ
ምን ይባላል ተመስገን እንጂ
ምን ይባላል አንተ ስትረዳ
ምን ይባላል ፍቅር እኮ ነህ
ምን ይባላል የማትከዳ (፪x)
አዝማች · Chorus
አባብዬ (፪x) አንተ እኮ ነህ እድል ፈንታዬ
አብትዬ (፪x) አንተ እኮ ነህ እድል ፈንታዬ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ