መቼ ተወኝ
Mech Tewegn
2009 · ትራክ 8 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
መራመድ ሲያቅተኝ በጽድቅ ጐዳና
ነፍሴም ስትጨነቅ በኀጢአት ፈተና
ሥጋዬም ሲረክስ ጠፍቶ ህሊናዬ
እንደሰው መች ተወኝ (፪x) ጌታዬ
ጨክኖ መች ተወኝ (፪x) ጌታዬ
ቁጥር 1 · Verse 1
መጠቋቆሚያ ሲያደርገኝ ሰው ሁሉ
እንግዲህ ተስፋም የለው እያሉ
መች ቀረሁ ወድቄ ተሸማቅቄ
ከአምላኬ ጉያ እንዲያው ርቄ
እንደገና አረገኝ ቀና
እንደገና አረገኝ ቀና (፪x)
አዝማች · Chorus
መራመድ ሲያቅተኝ በጽድቅ ጐዳና
ነፍሴም ስትጨነቅ በኀጢአት ፈተና
ሥጋዬም ሲረክስ ጠፍቶ ህሊናዬ
እንደሰው መች ተወኝ (፪x) ጌታዬ
ጨክኖ መች ተወኝ (፪x) ጌታዬ
ቁጥር 2 · Verse 2
ምህረትህን የለመደ አመለኛ
ተው ቢሉን የማይሰማ እልከኛ
ብለው ፈረዱ በእግዚአብሔር ፍቅር
በቸርነቱ ብዙ የተረዱ
የራሳቸውን ምሶሶ ትተው
የሰውን ጉድፍ የሚያዩ አጥርተው (፪x)
አዝማች · Chorus
መራመድ ሲያቅተኝ በጽድቅ ጐዳና
ነፍሴም ስትጨነቅ በኀጢአት ፈተና
ሥጋዬም ሲረክስ ጠፍቶ ህሊናዬ
እንደሰው መች ተወኝ (፪x) ጌታዬ
ጨክኖ መች ተወኝ (፪x) ጌታዬ
ቁጥር 3 · Verse 3
ይሄ ነው ብዬ የማልጨርሰው
ውለታ አለብኝ (፪x) ብዙ የማላውቀው
ይሄ ነው ብዬ የማልጨርሰው
ውለታ አለብኝ (፪x) ብዙ የማላውቀው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ