አንተ ባለአደራ
Ante Baleadera
2009 · ትራክ 6 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
"እንዲህም አላቸው 'ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ'" የማርቆስ ወንጌል ም. ፲፮ : ቁ.፲፭
አዝማች · Chorus
አንተ ባለአደራ ወዴት ነው ያለኸው
የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው
አንተ መልዕክተኛ ወዴት ነው ያለኸው
የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው
ተነስ መጽሓፉን አንሳ ፤ ተነስ ሚስጥሩን ግለጠው
ተነስ ግራ ለተጋባው ፤ ተነስ ልቡን አሳርፈው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የሕይወትን መንገድ አሳየኝ እያሉ
በጓዳቸው ሆነው ስንቶች ያለቅሳሉ አሄ
አንተ በዳንክበት መዳን አስባቸው
የእውነትን ቃል ይዘህ ሂድ ድረስላቸው እህ ሂድ ድረስላቸው
ብድራትህን ትኩር ብለህ ተመልከትና
የቀድሞው ነገር ትውስ ይበልህ እስኪ እንደገና
ያኔ የነበረው ትኩስ ፍቅርህ ዛሬም ቢቀና
ያቀናልሃል አምላክህ ደግሞ የአንተን ጐዳና
አዝማች · Chorus
አንተ ባለአደራ ወዴት ነው ያለኸው
የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው
አንተ መልዕክተኛ ወዴት ነው ያለኸው
የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው
ተነስ መጽሓፉን አንሳ ፤ ተነስ ሚስጥሩን ግለጠው
ተነስ ግራ ለተጋባው ፤ ተነስ ልቡን አሳርፈው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በሚብለጨለጨው ውበቷ ተማርከው
ስንቶች ሲኦል ገቡ ከምድር ተስማምተው አሄ
የሰማዩን ክብር የላዩን ሳያውቁ
መቃብር ወረዱ ሃያላን አለቁ እህህ ጠቢባን አለቁ
ወንጌሉን ይዘህ ሳትመሰክር ዘመን አለፈህ
ሰዉ እንደቅጠል በቀን በማታ እየረገፈ
መክሊቱን ቀብረህ ሳታተርፍበት ጌታ እንዳይመጣ
የተሰጠህን አደራ ይዘህ ፈጥነህ በል ውጣ አሄ
አዝማች · Chorus
አንተ ባለአደራ ወዴት ነው ያለኸው
የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው
አንተ መልዕክተኛ ወዴት ነው ያለኸው
የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው
ተነስ መጽሓፉን አንሳ ፤ ተነስ ሚስጥሩን ግለጠው
ተነስ ግራ ለተጋባው ፤ ተነስ ልቡን አሳርፈው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ