ዕልልታ ወጣ
Elelta Weta
2009 · ትራክ 1 · 4:47 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
አይቶልናል በከፍታ (፪x) የመረጠን ጌታ
ኧረ አይቶልናል በከፍታ (፪x) የመረጠን ጌታ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የምስኪኑ እምባ እንደፈሰሰ
መች ቀረ ታዲያ እሄው ታበሰ
ዛሬስ ተሰማ እንግዳ ነገር
ከጭቁኖቹ ከእነርሱ መንደር
ዕልልታ ወጣ አሃሃ ዜማ ፈለቀ
አስጨናቂያችን ጐልያድ ወደቀ (፪x) [1]
አዝማች · Chorus
አይቶልናል በከፍታ (፪x) የመረጠን ጌታ
ኧረ አይቶልናል በከፍታ (፪x) የመረጠን ጌታ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘመን ሲመጣ ታሪክ ሲቀየር
አይተናል እኛ ጌታ ሲያከብር
ብለን ዘመርን ተቀኘን ቅኔ
በአዲስ ምሥጋና ይዘን በገና
ዕልልታ ወጣ አሃሃ ዜማ ፈለቀ
አስጨናቂያችን ጐልያድ ወደቀ (፪x) [1]
አዝማች · Chorus
አይቶልናል በከፍታ (፪x) የመረጠን ጌታ
ኧረ አይቶልናል በከፍታ (፪x) የመረጠን ጌታ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ክረምት አለፈ ሃዘን መከራ
የድሆች አምላክ ደርሶ ሲራራ
ትዕቢተኛውን አዋረደ
ለእራሱ ክብር ሲሻ ምሥጋና
ዕልልታ ወጣ አሃሃ ዜማ ፈለቀ
አስጨናቂያችን ጐልያድ ወደቀ (፲x) [1]
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ