ጌታዬ እኮ ነው
Getayie Eko New
2009 · ትራክ 5 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታዬ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው
አምላኬ እኮ ነው ይህን ያደረገው
ወዳጄ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው
ኢየሱሴ እኮ ነው ይህን ያደረገው
እንዲህ እና እንዲያ ብዬ የምለው
ታሪክ የለኝም ታሪኬ እርሱ ነው(፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ጠላት እንዳሰበው በእኔ ቢሆንማ
የሞት አዋጅ ለቅሶ ነበር በተሰማ(፪x)
እንዳልጠፋ እንዳልሞት አስመለጠኝ ከሩቅ አይቶት
ግን እንዳልጠፋ እንዳልሞት አስመለጠኝ ከሩቅ አይቶት
አዝማች · Chorus
ጌታዬ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው
አምላኬ እኮ ነው ይህን ያደረገው
ወዳጄ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው
ኢየሱሴ እኮ ነው ይህን ያደረገው
እንዲህ እና እንዲያ ብዬ የምለው
ታሪክ የለኝም ታሪኬ እርሱ ነው(፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ያኔ በልጅነት ሳለሁ ብላቴና
አሳየኝ በምክሩ የጽድቅን ጐዳና(፪x)
እንዳልጠፋ እንዳልሞት አስመለጠኝ ከሩቅ አይቶት
ግን እንዳልጠፋ እንዳልሞት አስመለጠኝ ከሩቅ አይቶት
አዝማች · Chorus
ጌታዬ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው
አምላኬ እኮ ነው ይህን ያደረገው
ወዳጄ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው
ኢየሱሴ እኮ ነው ይህን ያደረገው
እንዲህ እና እንዲያ ብዬ የምለው
ታሪክ የለኝም ታሪኬ እርሱ ነው(፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
የማንም እጅ የለበትም እኔስ ለመኖሬ
በሕይወት እስከዛሬ (፪x)
እርሱ ነው ታሪኬ ፣ እርሱ ነው አምላኬ
እርሱ ነው ኑሮዬ ፣ እርሱ ነው ጌታዬ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ