Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አጠገቤ

Ategebie

2005 · ትራክ 8 · 6:02 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሀ ሁ ጌታ (፪x)

አጠገቤ ካለው ሰው ይልቅ

እርሱ ይቀርበኛል

መገኘቱ ህልውናው ይታወቀኛል (፪x)

ከውንድም ይልቅ ይጠጋጋኛል

ከእስትንፋሴ ይልቅ ይቀርበኛል

ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ (፬x)

በልቤ ያለህ ትልቅ ቦታ

ዘውትር ላክብርህ ሁሌ ጥዋት ማታ

ለእኔ ለእኔ አጠገቤ ካለው ሰው

ከሚነካኝ ከምነካው ከሚዳስሰኝ ከምዳስሰው

በዓይኑ ከሚያየኝ በዓይኔ ከማየው

እርሱ ለእኔ (፫x) ቅርቤ ነው

በገባሁበት አብሮ ይገባል

በሄድኩበት አብሮ ይሄዳል

እንደ እርሱ ያለ ወዳጅ

ታዲያ ከየት ይገኛል

አያያያያያያያ

እንደ እርሱ ያለ ወዳጅ

ታዲያ ከየት ይገኛል (፪x)

እርሱ ሰማይን ምድርን ሞልቷል

እንደ እርሱ ያለ ከየት ይገኛል

መኖሩንም ደስ በሚለው መንፈሱ ይገልጥልኛል (፪x)

አጠገቤ ካለው ሰው ይልቅ

እርሱ ይቀርበኛል (፪x)

ስፍራን አይመርጥም

ጊዜን አይመርጥም (፬x)

ሀ ሁ ጌታ (፪x)

አጠገቤ ካለው ሰው ይልቅ እርሱ ይቀርበኛል

መገኘቱ ህልውናው ይታወቀኛል (፪x)

ከውንድም ይልቅ ይጠጋጋኛል

ከእስትንፋሴ ይልቅ ይቀርበኛል

ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ ፣ ጌታ (፬x)

በልቤ ያለህ ትልቅ ቦታ

ዘውትር ላክብርህ ሁሌ ጥዋት ማታ

ታማኝ ወገኔ ያለኝ ከጐኔ

ታማኝ ወዳጄ ያለኝ በእጄ

በሄድኩበት ሁሉ የማትለየኝ

ታላቁ ጌታ የምትወደኝ

ታላቁ ኢየሱስ የምትመራኝ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ