ደሙ
Demu
2005 · ትራክ 4 · 6:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ክበርልኝ...ክበርልኝ
ደሙ ደሙ ደሙ
የጌታዬ ደም ነው ደሙ
ደሙ ደሙ ደሙ
የኢየሱስ ደም ነው ደሙ
ከኃጢአት ከበደሌ የነጻሁበት
እስራቴም ደግሞ የተበጠሰበት
በጐልጐታ ፈሶ ነጻ የወጣሁበት
ደሙ ደሙ ደሙ
የጌታዬ እኮ ነው ደሙ
ደሙ ደሙ ደሙ
የኢየሱስ ደም ነው ደሙ
አዝማች · Chorus
ኦ የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ
ኦ የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ
የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ቸርነት ምህረትህን እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ለእኔ የሆንከውን እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
ቁጥር 2 · Verse 2
አዝኜ ተክዤ በፍርሃት እያለሁ
በመስቀልህ ጉልበት ድፍረትን አገኘሁ
የፈሰሰው ደምህ ዛሬም ትኩስ ነው
ከብዙ እስራት ነጻ ሚያወጣ ነው
ነጻ ሚያወጣ ነው
አዝማች · Chorus
ኦ የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ
ኦ የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ
የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ቸርነት ምህረትህን እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ለእኔ የሆንከውን እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
ቁጥር 3 · Verse 3
የቀረኝ ምንድን ነው በሕይወቴ ላይ
የማትፈልገውን ፈጽሞ እንዳላይ
ጌታ ሆይ አንሳልኝ ከሕይወቴ ላይ
አንተው ግባበት በሩጫዬ ላይ
በሩጫዬ ላይ
ከዚህ በላይ ልኖርልህ እፈልጋለሁ
ከዚህ በላይ ላመልክህ እፈልጋለሁ
ጌታዬ ሆይ ንገረኝ ንገረኝ ምንድንነው
ኢየሱስ ጥሩ እየኖርኩልህ ነው ወይ ስታየኝ
ኢየሱስ አካሄዴ እንዴት ነው እስቲ ንገረኝ (፪x)
አዝማች · Chorus
ኦ የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ
ኦ የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ
የዓይኖቼ ማረፊያ ጌታ አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ቸርነት ምህረትህን እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
(አሃሃሃ) ለእኔ የሆንከውን እያየሁ
(አሃሃሃ) አመልክሃለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ