ስሙኝ እንጂ
Semugn Enji
2005 · ትራክ 14 · 6:02 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ስለ አንተ በጆሮዬ ከሰማሁት ይልቅ (፪x)
በዓይኔ ያየሁት ለእኔ ሆነብኝ ድንቅ (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ ተባረክ የእኔ ጌታ (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እግዚአብሔር ለምን እንዲህ አረክ አይባልም (፪x)
የሚሰራውን ያውቃል ፍፁም አይዘነጋም (፪x)
የእኔ ጌታ ተባረክ የእኔ ጌታ (፬x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋናዬ (፬x)
ይድረስ ለአንተ ብቻ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
እግዚአብሔር ህዝቡን መታደግን ያውቃል (፪x)
ካስፈለገ ደግሞ ፀሐይን ያቆማል (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ ተባረክ የእኔ ጌታ (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
እግዚአብሔር አምላኬ ጌታ ነው
ዓለም ሁሉ በሙሉ የእርሱ ነው (፪x)
አዝማች · Chorus
የእኔ ጌታ ተባረክ የእኔ ጌታ (፬x)
ቁጥር 5 · Verse 5
እግዚአብሔር አምላክን አትጠራጠሩት
ያደርጋል ብላችሁ በእውነት እመኑት
ስሙኝ እንጂ (፪x)
እግዚአብሔር አምላክን አትጠራጠሩት
ያደርጋል ብላችሁ በእውነት እመኑት
ስሙኝ እንጂ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
እስቲ ላስታውሳችሁ ትውስ አለኝ እኔም
አምላኬ የሰራው ከዚህ ቀደም
ስሙኝ እንጂ (፪x)
የኤርትራን ባሕር ኧረ ማን ከፈለው
ውኃውን እንደ ግድግዳ ኧረ ማን አቆመው
ስሙኝ እንጂ (፪x)
ቁጥር 7 · Verse 7
የመንፈስ የመንፈስ የመንፈሱን እንጂ
የሥጋውን መስማት ያስጥላል ከደጅ
ስሙኝ እንጂ (፪x)
በምድረ በዳ ላይ ይህን ያደርጋል
ከቶ ለምን አልከው አይቻለውም ወይ
ስሙኝ እንጂ (፪x)
አዝማች · Chorus
ምሥጋናዬ (፬x)
ይድረስ ለአንተ ብቻ ጌታዬ (፪x)
ቁጥር 8 · Verse 8
አቤት ውበቱ የተዓምራቱ
ለጠበቀው ሰው እስከ ሰዓቱ
ሊመጣ ሲልም አረፋፈዱ
ሊነጋ ሲልም መጨላለሙ
አርፍዶ ይነሳል ሁሉን ይቀድማል
የተዓምራቱን ውበት ያሳያል (፪x)
አቤት ውበቱ የተዓምራቱ
ለጠበቀው ሰው እስከ ሰዓቱ
ሊመጣ ሲልም አረፋፈዱ
ሊነጋ ሲልም መጨላለሙ
አርፍዶ ይነሳል ሁሉን ይቀድማል
የተዓምራቱን ውበት ያሳያል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ