Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለየት ያለ ነው

Leyet Yale New

2005 · ትራክ 7 · 5:50 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አላሳልፈኝ ያለው የብረት መዝጊያው

ኧረ እንዴት ተከፈተ አሁን በጊዜው (፪x)

ባለስልጣኑን ጌታ በእኔ ሲያየው

ለመከፈት መነካት አላስፈለገው (፪x)

አልፈራም ነገን ምን እሆን ብዬ

እኖራለሁ በእርሱ ተደላድዬ

አልሰጋም ነገን ምን እሆን ብዬ

እኖራለሁ በእርሱ ተደላድዬ

ኧረ ምን ችግር አለ

ጌታዬ እግዚአብሔር አለ (፪x)

ኧረ ምን ችግር አለ

እርሱ እግዚአብሔር አያለ

ኧረ ምን ችግር አለ

ጌታዬ እግዚአብሔር አለ

እሄዳለሁኝ ገና አላቋርጥም

በእኔ ያለው እርሱ ፍፁም አይደክምም (፪x)

በኃይልና በብርታት በእኔ ሳይሆን

በመንፈሱ በእግዚአብሔር ችላለሁ ሁሉን (፪x)

በእርሱ ታምኜ ምን እሆናለሁ

በትከሻው መሃል ላይ በክብር አድራለሁ (፪x)

ኧረ ምን ችግር አለ

ጌታዬ እግዚአብሔር አለ (፪x)

ኧረ ምን ችግር አለ

እርሱ እግዚአብሔር አያለ

ኧረ ምን ችግር አለ

ጌታዬ እግዚአብሔር አለ

እስቲ ልናገር ስለዚህ ጌታ አሃ

የጠላቴን ትጥቅ አቤት ሲያስፈታ (፫x)

አደራረጉ ከሰው ልዩ ነው ኦሆ

የእኔ እኮ ጌታ ለየት ያለ ነው ፤ ለየት ያለ ነው (፪x)

ቀን በቀን እኔ ማየው ቀን በቀን

የሚያሳየኝ ጉድ እኮ ነው ቀን በቀን

ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ በልጧል

የማዳን እጁ ለእኔ ቀርቧል (፪x)

ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ በልጧል

የማዳን እጁ ለእኔ ቀርቧል (፪x)

በተዐምር እወጣለሁ በተዐምር እገባለሁ

የታመንኩበት ጌታዬ ተዐምረኛ ነው (፪x)

አሁን አሁንማ ብሷል አሁን አሁን (፪x)

እኔም አምነዋለሁ እርሱም ይሰራል

ከተዐምራቱ እኔን ያጠግበኛል (፪x)

እኔም አምነዋለሁ እርሱም ይሰራል

ከተዐምራቱ እኔን ያጠግበኛል (፪x)

እስቲ ልናገር ስለዚህ ጌታ አሃ

የጠላቴን ትጥቅ አቤት ሲያስፈታ (፫x)

አደራረጉ ከሰው ልዩ ነው ኦሆ

የእኔ እኮ ጌታ ለየት ያለ ነው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ