Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

በዋጋ

Bewaga

2005 · ትራክ 4 · 6:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በዋጋ ገዛኸኝ እንዳልጠፋ እንዳልሞት (፪x)

በዋጋ ገዛኸኝ እንዳልጠፋ እንዳልሞት (፪x)

ሃዘን መከራዬን ረሳሁ

በፊቱ ሞገስ አገኘሁ (፪x)

ክብር ለእግዚአብሔር

ለዚህ መብቃቴ እንዲህ መሆኔ

በእርሱ ብርታት ነው መች በእኔ

ክብር ይድረሰው መድህኔ

ክብር ለእግዚአብሔር (፯x)

አይደለም በእኔ በእኔ በኃይሌ

አይደለም በእኔ በእኔ (፪x)

ቅንነትህ (፫x)

አሰረኝ አሰረኝ የዋህነትህ

አንተ ቅንና ቸር የዋህ

ትህትናን ለሁሉ አስተማርክ

ከሃጥያት በቀር ስለሰው

በነገር ሁሉ ተፈተንክ አሃ

ተፈተንክ

ቅንነትህ (፫x)

አሰረኝ አሰረኝ የዋህነትህ

የግሌ ነህ የእራሴ

የብቻዬ ጌታዬ ለእኔ (፪x)

አይደለም በእኔ በእኔ በኃይሌ

አይደለም በእኔ በእኔ

አይደለም በእኔ

ቅንነትህ (፫x)

አሰረኝ አሰረኝ የዋህነትህ

ክብሩ (፫x)

ለእግዚአብሔር ለእርሱ ይሁንለት

ስራዬን ሰራልኝ አገኘሁ ነጻነት

ድንቅ ነው (፫x)

ሥራው አቤት ሲችልበት

ጠላትን ማንበርከክ አቤት ሲችልበት

እግዚአብሔር ቀደመ ኦሆሆሆ

ጠላቴን ገጠመ ኡሁሁ

ደገመ ደገመ ኦሆሆሆ

ፊቴ እየቀደመ ኡሁሁ (፪x)

ኤልሻዳይ ነው እርሱ ለማን ይበገራል

እግዚአብሔርን አይቶ ጠላቴም ፈርቶኛል (፪x)

ይሄ ነው (፭x)

ጌታ ድል አድራጊው (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ