ፍቅርህ ነክቶኛል
Feqreh Nektognal
2005 · ትራክ 12 · 5:53 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ምህረትህና ቸርነትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል
እለት እለት ክቡር ደሙ ይሸፍነኛል ይጠብቀኛል
ሃሌሉያ ቤትህ ያገቡኛል
ታማኙ እጅህ መቼ ይጥላል
ቁጥር 2 · Verse 2
ታማኙ እጅህ ቤት ያደርሳል (፪x)
ሃሌሉያ ቤትህ ያገቡኛል
ቁጥር 3 · Verse 3
ዝም ዝም አትበል ነፍሴ ትለኛለች
የአምላኳን ውለታ ሁሌም ታስባለች (፪x)
እንዴት የምን ዝም ዝም ዝምታ
በልቤ ለሞላው ጌታ
ፍቅርህ ነክቶኛል ልመስክርልህ
ሰው ሁሉ ይወቅ ማያውቅ አለ እንዴ
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ እኔ አንተን ልውደድ
ቁጥር 4 · Verse 4
ሁልጊዜ አመልክሃለሁ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ሃሌሉያ በጣም እወድሃለሁ
ሁልጊዜ አመልክሃለሁ (፪x)
ቁጥር 6 · Verse 6
ሃሌሉያ በጣም እወድሃለሁ
እንዴት የምን ዝም ዝም ዝምታ
በልቤ ለሞላው ጌታ
ፍቅርህ ነክቶኛል ልመስክርልህ
ሰው ሁሉ ይወቅ ማያውቅ አለ እንዴ
አዝማች · Chorus
ሃሌሉያ እኔ አንተን ልውደድ
ቁጥር 7 · Verse 7
ያለፈው ዘመኔ አለፈ አለፈ
ዳግመኛ ላላየው
ያለፈው ኑሮዬ አለፈ አለፈ
ዳግመኛ ላላየው
ቀሪውን ዘመኔን ባርከው ባርከው
የአንተው ለአንተው አድርገው
ያለአንተ መኖር ከቶ አይሆንልኝም
ከእንግዲህ እንካ ተቆጣጠረኝ
ከእንግዲህ እንካ እንካ ጌታ ተቆጣጠረኝ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ