Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ጥንትም የረዳኝ

Tentem Yeredagn

2005 · ትራክ 13 · 5:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጥንት ለረዳኸኝ

አሁንም እንደምትረዳኝ

ሁሌም እንደምትረዳኝ አውቃለሁ

ስለዚህ ስለዚህ አመሰግንሃለሁ

ስለዚህ ስለዚህ አመሰግንሃለሁ (፪x)

ታምኜብህ በአንተ ሩጫዬን እቀጥላለው

የሚያቅተኝ ምንድን ነው እንዳልከኝ እሆናለው

ጌታዬ አንተን ይዣለሁ (፪x)

ከዓለም ዕዳ ልውጣ በዚያው ቀን የምትጠብቀኝ

እንደተናገርክ ጌታ እንዲሁ አደረክልኝ

እውነትህ ነው አዕምሮዬን ሰላምህ ገዛኝ

እውነትህ ነው አዕምሮዬን ተቆጣጠረኝ (፪x)

ጥንት ለረዳኸኝ

አሁንም እንደምትረዳኝ

ሁሌም እንደምትረዳኝ አውቃለሁ

ስለዚህ ስለዚህ አመሰግንሃለሁ (፪x)

እንዴት እወጣዋለው እንዴትስ አልፈዋለሁ

ብዬ ባልኩት ነገር ውስጥ የአንተን ትልቅነት አየሁ

እውነትህ ነው አዕምሮዬን ሰላምህ ገዛኝ

እውነትህ ነው አዕምሮዬን ተቆጣጠረኝ (፪x)

ጥንት ለረዳኸኝ

አሁንም እንደምትረዳኝ

ሁሌም እንደምትረዳኝ አውቃለሁ

ስለዚህ ስለዚህ አመሰግንሃለሁ (፪x)

ተራራና ዝቅታ በሕይወቴ ሲያልፉብኝ

እንዴት እንደወጣሁት ፈጽሞ አልታወቀኝ

እውነትህ ነው አዕምሮዬን ሰላምህ ገዛኝ

እውነትህ ነው አዕምሮዬን ተቆጣጠረኝ (፪x)

ማዕበልና ወጀቡ ሲያናውጡብኝ መርከቡን

ጌታ ተነሳ ገሰጸው አፈረሰበት ሃሳቡን

ወግድ ቁም አለው ቆመ ነገሩ

ጌታን ስለያዘው አያሰጥመውም አለው (፪x)

በላይ ክብር በታች ክብር

ጸንተህ ለምትኖር ለእግዚአብሔር

ክብር ይሁን ክብር (፬x)

የዜማ ዕቃ ይምጣ ሁሉም ለእርሱ ይሁን

አናግሩት መሰንቆውን ደርድሩት በገናውን

ክብር ይሁን ክብር (፪x)

ክብር ይሁን ክብር (፲፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ